ዳሸን ባንክ ከኢትዮጵያ ውጭ ለንግድ ሥራ የሚጓዙ ደንበኞቹ ግብይታቸውን በውጭ ምንዛሪ ለመፈጸም የሚያስችላቸው የዴቢት ካርድ ይፋ ሲያደርግ፣ አቢሲኒያ ባንክ ደግሞ ዓይነ ሥውራን የሚገለገሉበት ኤቲኤም አገልግሎት ላይ አዋለ፡፡ ሁለቱ ባንኮች ሐሙስ ጥቅምት 25 ቀን 2014 ዓ.ም. ይፋ ያደረጉዋቸው አዲሶቹ አገልግሎቶቻቸው በባንክ ኢንዱስትሪው ውስጥ ለመጀመርያ ጊዜ የሚተገበሩ ስለመሆናቸው ባንኮቹ በሰጡዋቸው መግለጫዎች አመልክተዋል፡፡ ዳሸን ባንክ አሜሪካን ኤክስፕሬስ የተሰኘውን …
አርች ኮልድ ሶልሽንስ ከ2.9 ቢሊዮን ብር በላይ የሆነ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክት በኢትዮጵያ ለመተግበር ፍላጎት ማሳየቱ ተጠቆመ
መሠረቱን በእንግሊዝ አገር ያደረገና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ድርጅቶች ድጋፍ የሚንቀሳቀስ አርች ኮልድ ሶልሽንስ የተባለ ድርጀት ከ2.9 ቢሊዮን ብር በላይ የሆነ የማቀዝቀዣ መጋዘን ግንባታ ኢንቨስትመንት ፕሮጀክት በኢትዮጵያ ለመተግበር ፍላጎት ማሳየቱ ተጠቆመ፡፡ ድርጅቱ በቂሊንጦ የኢንዱስትሪ ፓርክ የማቀዝቀዣ መጋዘን (የኮልድ ቼይን ፋሲሊቲ) የሚያቀርብ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፣ ይህም መድኃኒት፣ ምግብና ሌሎች ሊበላሹ የሚችሉ ምርቶችን በዝቅተኛ የአየር ሁኔታ እንዳይበላሽ ለማቆየት …
Government lifts tax on food items
In an effort to curb and control the rising inflation and enhance the purchasing capacity of the public, the government removed the tax levied on basic commodities such as wheat, edible oil, sugar and rice as of September 3, 2021. The Value Added Tax (VAT) that has been levied on items such as pasta, …
መርካቶዎች እየተፈተኑባቸው ያሉ ችግሮች
ከሁለት አሠርት በላይ በንግድ ላይ ለተሰማራው አቶ ቴድሮስ ፍቅሩ፣ መርካቶ ማለት ከሰፈርም ከመነገጃነትም በላይ ነው። ‹‹ተወልጄ አድጌ ሀብት ያፈራሁባት ልዩ ሥፍራ ናት›› በማለት መርካቶን ያወድሳል የ43 ዓመቱ ጎልማሳ አቶ ቴድሮስ። በልብስ ምርቶች ንግድ፣ በቤትና ቢሮ ዕቃዎች ማምረትና መሸጥ ላይ የተሰማራው አቶ ቴድሮስ፣ በመርካቶ ሕይወቱን ከልጅነት እስከ አዋቂነት ቢያሳልፍም በመዲናዋ ነግዶ ሀብት ማፍራት ቀላል እንዳልሆነ ያነሳል። ‹‹ምንም እንኳን መርካቶ ለመላው ኢትዮጵያውያን ምርት የሚከፋፈልባትና የሚቀርብባት የሁላችንም የገበያ መዲና ብትሆንም፣ ከቀን ወደ ቀን ሠርቶ መለወጥ እየከበደ ነው›› የሚለው አቶ ቴድሮስ፣ ለዚህም መንግሥትና ሕገወጥ ነጋዴዎችን ይወቅሳል። ከ30 ሺሕ በላይ ሱቆችና ከ700 ሺሕ በላይ ሸማቾች፣ ነጋዴዎችና የንግድ ሠራተኞች በየቀኑ ገብተው ይወጡባታል ተብሎ በምትታመነው መርካቶ፣ የተለያዩ ችግሮችን መመልከት አዲስ ነገር አይደለም። ከሌባና ቀማኞች ገንዘብና ንብረታቸውን ለመጠበቅ ከሚሞክሩ ሸማቾች እስከ በሙስና የተዘፈቁ አንዳንድ የገቢዎች ሠራተኞች ለመሰወር የሚሞክሩ ሠራተኞችን ማየት የተለመደ ጉዳይ ነው። ሁሉም ዓይነት ነጋዴዎች በየፊናቸው እንደ ዘርፋቸው ሁኔታ የተለያዩ ተግዳሮቶች ቢገጥማቸውም ሪፖርተር በመርካቶ በመገኘት ባደረገው ዳሰሳ በአብዛኛው የሚያነሱት ቅሬታዎች ፍትሐዊ የንግድ ሥርዓት አለመኖር፣ ለሙስና በር የከፈተ የተጨማሪ እሴት ታክስ አተገባበርንና የመሠረተ ልማቶች አለሟሟላትን ነው። ‹‹የፍትሐዊንግድያለ›› የፌዴራልም ሆነ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንዲሁም የወረዳ ንግድ ቢሮዎች የተገልጋዮች ቻርተር ላይ በጉልህ ከተቀመጡ ጉዳዮች አንዱ ፍትሐዊ፣ ግልፅና በውድድር ላይ የተመሠረተ የንግድ ሥርዓትን ማስፈን ነው። ይህንንም መተግበር ከመንግሥት አጀንዳዎች መካከል መሆኑን የመንግሥት ባለሥልጣናት በተደጋጋሚ ያነሳሉ። ይሁን እንጂ የተጻፈው አልያም የተወራው ከትግበራው አኳያ ፈፅሞ የተለየ መሆኑን ነጋዴዎች ይናገራሉ። በመርካቶ አመዴ ተራ በጫማ ችርቻሮ ንግድ ላይ የተሰማሩት አቶ አማኑኤል መንግሥቱ እንደሚናገሩት፣ የንግድ ሥርዓቱ ላይ የፍትሐዊነት ችግሮች መታየት ከጀመሩ ሰንበትበት ብለዋል። የመንገድ ላይ ንግድ መስፋፋትን እንደ ማሳያ የሚያነሱት አቶ …