ሃቢታት ፎር ሂውማኒቲ ኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ያገለገለ ተሸከርካሪ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

habitat-for-humanity-ethiopia-HFE-logo-1

Overview

  • Category : Vehicle Sale
  • Posted Date : 12/19/2022
  • Phone Number : 0116600195
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 12/27/2022

Description

      የጨረታ ማስታወቂያ

ሃቢታት ፎር ሂውማኒቲ ኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ያገለገለ ተሸከርካሪ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

1. የተሸከርካሪውን ሁኔታ ማየት ለሚፈልጉ ተጫራቾች ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ4፣የውሃ እና መስኖ ልማት ኢነርጂ ሚኒሰትር 22 አካባቢ ከካፒታል ሆቴል በስተጀርባ በኩል የሚገኘው ሊሉ (LILU) ህንጻ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና ጽ/ቤት ባለው የመኪና ማቆሚያ ቦታ ከታህሳስ10/2015 ዓም እስከታህሳስ17/2015 ዓም ድረስ ዘወትር በስራ ሰዐት ከ2፡30 እሰከ 6፡00 እና ከ7፡30 አስከ 10፡30) መመልከት ይቻላል፡፡

2.ስለአሻሻጡ የተዘጋጀውን የተሸከርካሪው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልጽ የጨረታ ሠነድ መመሪያ እንዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያውን ቅጽ የማይመለስ ብር150.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር) ከላይ በተገለጸው የሃቢታ ፎር ሂውማኒቲ ኢትዮጵያ የድርጅቱ ፋይናንስ ቢሮ በመምጣት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዐት ከታህሳስ10ቀን/2015ዓም እስከ ቀን ታህሳስ16ቀን/2015ዓም እስከ ቀኑ 9፡00ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡

3.ተጫራቹ መግዛት የሚፈልጉትን ያገለገለው ተሸከርካሪ ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ታህሳስ 17ቀን /2015ዓም እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዐት ድረስ ብቻ ከላይ በተገለጸው የድርጅቱ ጽ/ቤት አድራሻ በመገኘት የጨረታ ሰነድ አቅራቢዎች ዝርዘር ላይ በመመዝገብ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

4. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ 20በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ጨረታ ከመከፈቱ በፊት በታሸገው ኤንቨሎፕ ውስጥ በማስገባት ማቅረብ አለባቸው፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡ አሸናፊ ለሆኑት የጨረታ ማስከበሪያ በሚከፍሉት ዋጋ ውስጥ የሚታሰብ ይሆናል፡፡ ለተሸነፉ ተጫራቾች የጨረታ ግምገማ ውጤት ከተገለጸ ቦኋላ ሲፒኦ ተመላሽ ይደረጋል፡፡

5.ጨረታው ታህሳስ17ቀን/2015ዓም ከቀኑ በ6፡00ሰ0ት ተዘግቶ በዚያኑ ዕለት ማለት ታህሳስ17ቀን/2015ዓም ከቀኑ በ8፡00 ሰዐት በሃቢታት ፎር ሂውማኒቲ ኢትዮጵያ ዋና መስሪያ ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

6. የተጫራቾች አሸናፊው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ የጨረታ አሸነፊው በ10ቀናት ከፍለው በ15 ቀናት ውስጥ ንብረቱን የማንሳት ግዴታ አለበት፡፡

7.በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ካላነሳ ያስያዘው ገንዘብ ተመላሽ አይሆንም፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡ ከአሸናፊነቱም ይሰረዛል፡፡

8. በጨረታ ያሸነፈው ተጫራች የመኪናውን ማጓጓዣ፣ የማስጫኛ እና ልዩ ልዩ ወጪዎች በጨረታ አሸናፊው የሚከፈል ይሆናል፡፡

9.ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0116 600195 በመደወል ወይም በተጠቀሰው አድራሻ በግንበር ቀርቦ መጠየቅ ይቻላል፡፡

10. መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡