ሃያት ሬጀንሲ ለሆቴሉ ፍላጎት የሚውሉ ዕቃዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : Purchases
- Posted Date : 04/19/2021
- Phone Number : 0115171237
- Source : Reporter
- Closing Date : 04/30/2021
Description
የሀገር ውስጥ የግዢ ጨረታ ማስታወቂያ
ሆቴላችን ሃያት ሬጀንሲ ለሆቴሉ ፍላጎት የሚውሉ ዕቃዎች አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ ፍላጎት ያላቸውን ድርጅቶች አወዳድሮ በውል የአቅርቦት ስምምነት ማድረግ ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አይነትማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶች ሃያት ሬጀንሲ አዲስ አበባ በመስቀል አደባባይ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ፊትለፊት ባለው የሆቴላችን የዕቃ ማስረከቢያ በር በመምጣት የማይመለስ ብር አንድ መቶ ( 100)በመክፍል የጨረታውን ዝርዝር ወይም የእቃዎቹን ዝርዝር መውሰድ ይችላሉ፡፡
ተጫራች ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች የታደሰ የንግድ ፈቃድ ” የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ቲን ሰርተፍኬት ከጨረታው ሰነድ ጋር በታሸገ ፖስታ የመረጡትን አይነት ወይም ካታጎሪ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ
የእቃዎቹን ዝርዝር አይነት ፡-
ሀ. ደረቅ ምግቦች ወይም የግሮሰሪ አይተሞች እና የባልትና ውጤቶች ለ ስጋ የዶሮ የበግ የበሬ የፍየል የመሳሰሉት የስጋዎች እቅርቦቶች
ሐ የሀገር ውስጥ አሳዎች እና ከውጪ የመጡ ሲ ፉድ መ ፍራፍሬ እና አትክልቶች
ሠ እስቴሽነሪ እና ፕሪንቲንግ ረ ኬሚካልስ
ሸ ዩቲሊቲ ለምሳሌ ናፍጣ ” ኤልፒጂ ጋዝ እና የመሳሰሉትን ቀ የተለያዩ የአልኮል መጠጦች
በ ወተት እና የወተት ተዋፆ
ተጫራቾች ከላይ በተዘረዘረው መሰረት ጨረታቸውን እንዲያቀርቡ እያሳሰብን ከላይ የተዘረዘረውን የማያሟሉ ከጨረታው ይሰረዛሉ፡፡
ጨረታው ለ10 የስራ ቀናት ክፍት ሲሆን ተጨራቾች በስራ ሰአት ጠዋት ከ2-6- ከሰአት 7-11 ባለው ሰአት ከላይ በተጠቀሰው የድርጅቱ መግቢያ በር ብቻ ጨረታውን እንዲያስገቡ እናሳውቃለን፡፡
ሃያት ሬጀንሲ አዲስ አበባ ይሄንን ጨረታ በሙሉም ይሁን በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለማንኛወም መረጃ በስልክ ቁጥር +251 115171237 ግዢ ክፍል ብለው መደወል ይችላሉ፡፡