ህሊና ገንቢ ምግቦች ኃላ/የተ/የግል ማህበር ያገለገለ ተሸከርካሪ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Hilina-enriched-food-logo-1

Overview

  • Category : Vehicle Sale
  • Posted Date : 08/27/2022
  • Phone Number : 0116679041
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 09/09/2022

Description

ህሊና ገንቢ ምግቦች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

ህሊና ገንቢ ምግቦች ኃላ/የተ/የግል ማህበር ለህፃናትና ለአቅመ ደካሞች በጣም አስፈላጊና ወሳኝ የሆነ ምርት በማምረት የሚታወቅ በአገሪቱ ብቸኛ ድርጅት ነው፡፡

ድርጅታችን ያገለገለ ተሸከርካሪ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

የተሸከርካሪው ዓይነት ሊፋን አነስተኛ ሚኒባስ

ዝርዝር መግለጫ፡-              

የቻንሲ ቁጥር                   KMJTG18VP9C002577

የሞተር ቁጥር                   D6AV9169774

የሰሌዳ ቁጥር                   03-37385 ኢ.ት

የተሰራበት አገር                ኮርያ

የተሰራበት ዘመን           2009

የሚይዘው የሰው ብዛት        61

የባለቤትነት መታወቂያ ቁጥር         E0106233

የመነሻ ዋጋ                    ብር 1,450,000.00 (ብር አንድ ሚሊየን አራት መቶ ሀምሳ ሺህ)

ተሸከርካሪው የሚገኝበት ቦታ          ሕሊና ገንቢ ምግቦች ኃላ/የተ/የግ/ማህበር

በመሆኑም፡-

1ኛ) ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ኛውን ትክክለኛነቱ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ በማስያዝ ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ በመገኘት መወዳደር ይቻላሉ፡፡

18VP

2ኛ) ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ ቀናት በስራ ሰዓት ለገጣፎ በሚገኘው ፋብሪካችን ድረስ በግንባር ቀርበው የሚገዙበት ዋጋ በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ያስገባሉ፡፡

3ኛ) ጨረታውን ላላሸነፈ ተጫራች ያስያዘው ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስለታል፡፡

4ኛ) የጨረታው አሸናፊ በ5 /አምስት/ ቀናት ውስጥ ቀሪውን ገንዘብ ከፍሎ ተሸከርካሪውን መውሰድ አለበት፡፡

5ኛ) ተሸከርካሪውን በገዢው ስም እንዲዛወር ድርጅቱ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል፡፡

6ኛ) ለስም ማዛወሪያ የሚያስፈልገው ማንኛውንም ወጪ ገዢው ይሸፍናል፡፡

7ኛ) በተሸከርካሪው ሽያጭ ላይ የሚጠየቀው ተጨማሪ እሴት ታክስ ገዢ ይከፍላል፡፡

8ኛ) ጨረታው በማስታወቂያ በወጣ በ10ኛው ቀን ከቀኑ በ11፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ11ኛው ቀን ከጥዋቱ በሦስት ሰዓት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

9ኛ) ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡

አድራሻ  – ከአዲስ አበባ ከተማ በስተምስራቅ በኩል ደሴ መንገድ

ለገጣፎ ከተማ  –  ሮፓክ ፊት ለፊት

          ስልክ 0116 67 90 41/0116 67 90 06

ፋክስ 0116 67 90 19