ሆራይዘን ፕላነቴሽንስ ኃ/የተ/የግ/ማ ሸገር ዳቦ ማምረቻ የተለያዩ ተረፈ ምርቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

horizon-plantation-reportertenders-logo

Overview

  • Category : Other Sale
  • Posted Date : 10/23/2022
  • Phone Number : 0114626116
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 11/04/2022

Description

ሆራይዘን ፕላንቴሽንስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

ሸገር ዳቦ ማምረቻ

የጨረታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን ሆራይዘን ፕላነቴሽንስ ኃ/የተ/የግ/ማ ሸገር ዳቦ ማምረቻ የተለያዩ ተረፈ ምርቶችን ማለትም እንቅጥቃጭ ደረጃ አንድ እና ደረጃ 2፣ ገለባ (አነስተኛ መጠን ዕህል ያለው) ደረጃ አንድ እና ደረጃ 2 ፣ ንጹ ገለባ፣ አፈርቻ(አቧራ)ደረጃ አንድ እና ደረጃ 2 ፣እረጃጅም ገለባ፣ ጥራጊ ዱቄት፣የዳቦ ተረፈ ምርት ሊጥ ፣የተሰባበር ዳቦ ፣ጥቅም ላይ የዋለ ከረጢት(ማዳበሪያ) እና ጥቅም ላይ የዋለ የዘይት ጀሪካን(ባለ 20ሊትር) በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በዘርፉ የተሰማራቹ በሙሉ፡-

  1. የዘመኑን ግብር የከፈላቹ እና የንግድ ፍቃድ ያሳደሳቹ ድርጅቶች በጨረታው ላይ እንድትሳተፉ እየጋበዝን ለእያንዳንዱ ተረፈ ምርት በተናጠል የምትገዙበትን የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ከድርጅቱ በ100 ብር በመግዛት እና በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ማረሚያ ቤት ሳይደርስ በሚገኘው ፋብሪካችን በአካል በመቅረብ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ጨረታው የጨረታ ማስገቢያ ቀን ካበቃበት ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ላይ ተጫራቶች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/በተገኙበት ይከፈታል፤ ሆኖም ተጨራቾች በመክፈቻ ዕለትና ሰዓት አለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያግድም፡፡

ተጫራቶች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ 10,000 (አስር ሺ) ብር በድርጅቱ ስም(Horizon plantations plc) የተዘጋጀ ሲ.ፒ.ኦ ማሲያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

ማሳሰቢያ፡- የምታስገቡት ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ በፊት መሆን አለበት

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ

በስልክ ቁጥር +251 11 462 6116/80 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ