ሆፕ ኢንተርፕራይዝ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ከትምህርትና ስልጠና የጤና መድን ሽፋን ከአቅራቢ ድርጅቶች አወዳድሮ መግዛት የሚፈልግ ሲሆን የጤና መድን ሽፋኑ አጠቃላይ ጤና ፣ የአይን ፣ የጥርስ ፣ የአደጋና የሞት የመድህን ሽፋኖችን የሚያካትት እንዲሆን ይፈለጋል፡፡

Hope-Enterprises-Logo

Overview

  • Category : Insurance Services
  • Posted Date : 11/07/2022
  • Phone Number : 0974176600
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 11/18/2022

Description

ድርጅታችን ሆፕ ኢንተርፕራይዝ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ከትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን የእውቅና ፈቃድ አግኝቶ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ጀሞ አካባቢ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ደረጃ በተለያዩ   የትምህርት ዘርፎች ጥራት ያለው ትምህርት በመስጠት ላይ የሚገኝ የትምህርት ተቋም ነው፡፡

በመሆኑም በአሁኑ ጊዜ ለ113 ለሚሆኑ ቋሚ ሰራተኞች የጤና መድን ሽፋን ከአቅራቢ ድርጅቶች አወዳድሮ መግዛት የሚፈልግ ሲሆን የጤና መድን ሽፋኑ አጠቃላይ ጤና ፣ የአይን ፣ የጥርስ ፣ የአደጋና የሞት የመድህን ሽፋኖችን የሚያካትት እንዲሆን ይፈለጋል፡፡

ስለሆነም ይህንን አገልግሎት ለመስጠት የምትችሉ የመድህን ድርጅቶች (ኢንሹራንስ ካምፓኒዎች) ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 የሥራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ጀሞ 1 ለቡ መድሃኒአለም ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ከሚገኘው ድርጅታችን ፋይናንስ ቢሮ በአካል መጥታችሁ እንድትገዙ አናሳውቃለን፡፡

አጫራቹ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0974 17 66 00 ወይም 011 8 32 59 93