ለሂጅራ ባንክ አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

Announcement
Hijra-Bank-S.C-logo

Overview

 • Category : Announcement
 • Posted Date : 11/09/2022
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 12/04/2022

Description

የስብሰባ ጥሪ

ለሂጅራ ባንክ . ባለአክሲዮኖች በሙሉ

 አድራሻ፡-ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 09

የንግድ ምዝገባ ቁጥር፡ MT/AA/3/0052401/2013  

ካፒታል፡ 979,934,000

በኢትዮጵዯ ንግድ ሕግ አንቀጽ 366(1)፣367(1)393 እና 394 እንዲሁም በባንኩ መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 10 መሠረት የሂጅራ ባንክ አ.ማ 2ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ እሁድ ህዳር 25 ቀን 2015 ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል፡፡ በመሆኑም ባለአክሲዮኖች ወይም ወኪሎቻቸው በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት በጉባዔው ላይ እንዲገኙ የዳይሬክተሮች ቦርድ በአክብሮት ጥሪውን ያቀርባል፡፡

 1. የጉባዔው አጀንዳዎች
 2. የጉባዔውን አጀንዳዎች ማጽደቅ፤
 3. ምልዓተ ጉባዔው መሟላቱን ማረጋገጥ፤
 4. የጉባዔውን ድምጽ ቆጣሪዎች መሰየም፤
 5. እ.ኤ.አ የ2021/2022 ሂሳብ ዓመት ዓመታዊ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርትን ማዳመጥ፤
 6. እ.ኤ.አ የ2021/2022 ሂሳብ ዓመት የውጪ ኦዲሮችን ሪፖርት ማዳመጥ፤
 7. በተራ ቁ.4 እና 5 በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ ተወያይቶ ሪፖርቶቹን ማጽደቅ፤
 8. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት አስመራጭ ኮሚቴ መሰየም፤
 9. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት የምርጫ አፈጻጸም መመሪያ ማጽደቅ፤
 10. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምርጫ ማከናወን፤
 11. የጉባዔውን ቃለ-ጉባዔ ማጽደቅ፤

ማሳሰቢያ:-

 • ባለአክሲዮኖች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ለስብሰባ በሚመጡበት ጊዜ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፣ ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ ዋናውን እና አንድ ኮፒ ይዘው መቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 • በጉባኤው ላይ በግንባር መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች በንግድ ሕጉ አንቀፅ 373 መሠረት በወኪሎቻቸው መሳተፍ የሚችሉ ሲሆን፤ ጉባዔው ከመካሄዱ ከሶስት የስራ ቀናት በፊት ኦሎምፒያ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ህንጻ 3ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የባለአክሲዮኖች ክፍል ወይም በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የባንኩ ቅርንጫፍ ቀርበው ለዚሁ ጉዳይ የተዘጋጀውን የውክልና መስጫ ቅጽ በመፈረም ወይም ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው አካል በስብሰባው ለመገኘት የሚያስችል የተረጋገጠ የውክልና ስልጣን ማስረጃ በያዘ ተወካይ አማካኝነት በጉባዔው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
 • በውል እና ማስረጃ ጽ/ቤት የተረጋገጠ የውክልና ማስረጃ የያዘ ተወካይ ዋናውን ማስረጃ እና ኮፒውን፣ የወካዩን ኢትዮጵያዊነት ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ የውጭ ሀገር ዜጋ መሆኑን የሚያረጋግጥ የታደሰ መታወቂያ፣ ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ ኮፒ ይዘው መቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

 የዳይሬክተሮች ቦርድ

ሂጅራ ባንክ .