ለሔልዝ ኤንድ ሆልነስ ኢትዮጵያ ድርጅት ሲገለገልበት የነበረ ያገለገለ ተሽከርካሪ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Overview

 • Category : Vehicle Sale
 • Posted Date : 11/07/2022
 • Phone Number : 0918712323
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 11/18/2022

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ለሔልዝ ኤንድ ሆልነስ ኢትዮጵያ ድርጅት ሲገለገልበት የነበረ ያገለገለ ተሽከርካሪ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ፡

ተጫራቾች

 1. ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በወጣ በ5ኛው ቀን ተሽከርካሪዉ በሚገኝበት አድራሻ ልደታ ቤተክርስታን አካባቢ መኪና ማቋሚያ ቦታ ከጠዋቱ 3፡30 እስከ 9፡30 ሰዓት ድረስ መመልከት ይችላሉ፤
 2. ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረት ጠቅላላ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) አሰርተው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፣
 3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ለአሸናፊዎች ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊዎች የጨረታው ውጤት በጸደቀ በ 3 (ሶስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ይመለስላቸዋል ፡
 4. ተጫራቾች ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ሰባት ተከታታይ የስራ ቀናት ስባት/7/ ውስጥ የጨረታውን ሰነድ ማስገባት አለባቸው፡፡ በአስረኛ ቀን የጨረታ ሰነዱ የሚገባው እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ይሆናል፡፡
 5. አሸናፊ ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸውን ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ3 ተከታታይ የስራ ቀናት ውሰጥ ገንዘቡን ገቢ በማድረግ በ5 ተከታታይ የሰራ ቀናት ውሰጥ ንብረቱን የመረከብ ግዴታ አለባቸው ይህ ካልሆነ ያስያዙት ገንዘብ ወይም ሲፒ.ኦ. ለሔልዝ ኤንድ ሆልነስ ኢትዮጵያ ድርጅት ገቢ ይሆናል፡፡
 6. ተጫራቾች ከሔልዝ ኤንድ ሆልነስ ኢትዮጵያ ድርጅት ግዢና ፋይናንስ የንብረቶቹን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ 150 /አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ እየከፈሉ ማስታወቂያው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ሰባት /7/ ተከታታይ የስራ ቀናት ድረስ መግዛት የሚችሉ ሲሆን በሰባተኛዉ ቀን ሰነዱ የሚሸጠው አስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ይሆናል፡፡
 7. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ሰባት /7/ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ10ኛው ቀን ከጧቱ 4፡00 ሰአት ተዘግቶ በዚያው ቀን 4፡30 የተጫራቾቹ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ለሔልዝ ኤንድ ሆልነስ ኢትዮጵያ ድርጅት ቢሮ ይከፈታል፡፡
 8. ተጫራቾች ስለ አሻሻጡ ዝርዝር ሁኔታ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ከተያየዘው የተጫራቾች መመሪያ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
 9. አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፣
 10. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመስረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 11. ማንኛውም ወጪ በገዥ የሚሸፈን ይሆናል፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ

በሞባይል ስልክ ቁጥር፡+251 918 71 23 23

             የቢሮ ስልክ ፡+251 118 21 16 21

       ሔልዝ ኤንድ ሆልነስ ኢትዮጵያ ድርጅት