ለራይደርስ ትሬዲንግ እና ማኑፋክቸሪንግ አክሲዮን ማኅበር ባለአክሲዮኖች በሙሉ

Announcement

Overview

 • Category : Announcement
 • Posted Date : 11/07/2022
 • Phone Number : 0960551010
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 11/27/2022

Description

ለራይደርስ ትሬዲንግ እና ማኑፋክቸሪንግ አክሲዮን ማኅበር ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ራይደርስ ትሬዲንግ እና ማኑፋክቸሪንግ አክሲዮን ማኅበር በኢትዮጵያ የንግድ ሕግ አንቀጽ 393 እና 394 እንዲሁም በአክሲዮን ማኅበሩ መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 10 መሠረት የባለአክሲዮኖች 1ኛ መደበኛ እና 2ተኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ እሑድ ህዳር 18 ቀን 2015 ከቀኑ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ ባንቢስ ሱፐር ማርኬት አጠገብ በሚገኘው ዲ ሊኦፖል ሆቴል የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይካሔዳል፡፡ ስለሆነም በስብሰባው ላይ በአካል ወይም በሕጋዊ ወኪሎቻችሁ አማካኝነት እንድትገኙ በአክብሮት ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

የእለቱ የስብሰባው አጀንዳዎች

 1. የስብሰባውን ድምፅ ቆጣሪዎች መሰየምና ምልዓተ ጉባኤ መሟላቱን ማረጋገጥ
 2. ከቤቱ የሚነሱ አጀንዳዎችን ማካተት እና የእለቱን የስብሰባ አጀንዳዎች ማጽደቅ
 3. የ2014በጀት ዓመት የአክሲዮን ማኅበሩ የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ማድመጥና ማጽደቅ
 4. የ2014በጀት ዓመት የአክሲዮን ማኅበሩን የኦዲት ሪፖርት ማድመጥና ማጽደቅ
 5. የውጭ ኦዲተርን መሰየምና ማጽደቅ
 6. አዲስ አባል በመቀበል የማህበሩን ካፒታል ስለማሳደግ
 7. ለነባር አባላት በጥሬ ገንዘብ መዋጮ ካፒታል ስለማሳደግ
 8. በተጓደለ የተቆጣጣሪ ቦርድ አባል ምትክ አዲስ አባል መሾም እና ማፅደቅ

ማሳሰቢያ

 • በጉባኤው ላይ የሚገኙ ባለአክሲዮኖች የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ /ማስክ/ ማድረግ እና ሌሎች የጥንቃቄ እርምጃዎችን መከተል ይጠበቅባቸዋል፡፡ እንዲሁም ለስብሰባው ሲመጡ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ ዋናውንና ኮፒ ይዘው መምጣት ይኖርቦታል፡፡
 • በጉባኤው ላይ መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ጉባኤው ከመካሄዱ በፊት ሳር ቤት ጂ ኤፍ ኬ አፓርታመንት ምድር ላይ በሚገኘው የአክሲዮን ማኅበሩ ቢሮ በአካል በመገኘት የውክልና ቅጽ በመሙላት ውክልና መስጠት የምትችሉ ሲሆን ተወካዮቻችሁ በሰነዶች ማረጋገጫ መ/ቤት የተረጋገጠ የውክልና ፎርሙን ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን እንዲሁም የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ ይዘው እንዲቀርቡ በማድረግ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡
 • ተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮቻችን +251960551010 /+251931999999 ማግኘት ይቻላል፡፡

ራይደርስ ትሬዲንግ እና ማኑፋክቸሪንግ አ.ማ