ለሲዳማ ባንክ አ.ማ ባለ አክሲዮኖች የተላለፈ የጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ

Sidama-Bank-sc-logo

Overview

 • Category : Announcement
 • Posted Date : 11/21/2022
 • Phone Number : 0462123591
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 12/17/2022

Description

 ማስታወቂያ

ለሲዳማ ባንክ አ.ማ ባለ አክሲዮኖች

የተላለፈ የጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ

ባንኩ በአዲሱ የንግድ ሕግ አንቀጽ 367፣ 393(2) እና 400 እንዲሁም በባንኩ መመስረቻ ጽሁፍ አንቀጽ 10(5 እና 6) መሰረት 24ኛ መደበኛ እና 8ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤዎችን ቅዳሜ ታህሳስ 8 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ በሀዋሳ ከተማ በሚሊኒየም አዳራሻ ስለሚያካሂድ ባለ አክሲዮኖች በአካል ወይም በሕጋዊ ወኪል አማካይነት በጉባኤ ላይ እንዲሳተፉ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

የ24ኛ መደበኛ ጉባኤ አጀንዳዎች፡-

 1. የዳይሬክተሮች ቦርድ እ.ኤ.አ 2021/2022 በጀት ዓመት በቀድሞ የሕግ ሰውነት የተከናወነ ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት መስማትና ማጽደቅ
 2. የውጭ ኦዲተሮችን እ.ኤ.አ 2021/2022 በጀት ዓመት በቀድሞ የሕግ ሰውነት የተከናወነ ዓመታዊ የኦዲት ሪፖርት መስማትና ማጽደቅ
 3. ቀሪ የአክሲዮን ክፍያ ማጠናቀቂያ ጊዜን መወሰን
 4. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን እ.ኤ.አ የ2022/2023 በጀት ዓመት ወረሃዊና ዓመታዊ ክፍያዎችን መወሰን
 5. የውጭ ኦዲተሮችን ለቀጣይ ሶስት በጀት ዓመታት (እ.ኤ.አ ከ2022/2023 – 2024/2025) መሾምና ክፍያቸውን መወሰን
 6. የጉባኤውን ቃለ-ጉባኤ ማጽደቅ

የ8ኛ አሰቸኳይ ጉባኤ አጀንዳዎች፡-

 1. የባንኩን መመስረቻ ጽሁፍና መተዳደሪያ ደንብ ማሻሻል
 2. የጉባኤውን ቃለ-ጉባኤ ማጽደቅ

በጉባኤዎቹ በአካል የሚገኙ ባለ አክሲዮኖችም ሆነ ወኪሎች ማንነታቸውን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም መንጃ ፍቃድ መያዝ እንዳለባቸው እናሳስባለን፡፡

በጉባኤው ላይ በአካል መሳተፍ የማይችሉ ባለ አክሲዮኖች አግባብነት ባለው አካል በተሰጠ ሕጋዊ ውክልና ወይም በባንኩ የተዘጋጀውን የውክልና ቅጽ በሀዋሳ ከተማ ሂጣታ ቀበሌ በሚገኘው ከባንኩ ዋና መ/ቤት 6ኛ ፎቅ ወይም በአዲስ አበባ ከተማ ግሎባል ሆቴል ፊት ለፊት ባለው ሚኪዎር ፕላዛ ሕንጻ 3ኛ ፎቅ በሚገኘው የባንኩ አገናኝ ቢሮ ከህዳር 25 – ታህሳስ 7/2015 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በመሙላት በወኪል አማካይነት መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ባንኩ ከዛሬ 24 ዓመት በፊት ከተመሰረተው ከሲዳማ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ ወደ ባንክ የተሸጋገረ ኩባንያ ሲሆን በንግድ መዝገብ ቁጥር MT/AA/10/0053062/2014፣ በባንክ ሥራ ፍቃድ ቁጥር LLB/TM/031/2022፣ በተፈረመ ካፒታል ብር 1.4 ቢሊዮን እና በተከፈለ ካፒታል ብር 574.8 ሚሊዮን እ.ኤ.አ ከጁላይ 1/2022 ጀምሮ ፈቃድ አግኝቶ እየሰራ የሚገኝ ነው፡፡

ሲዳማ ባንክ አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ

ለተጨማሪ መረጃ፡

የባንኩን ድረ-ገጽ፡ https://sidamabanksc.com/ ወይም የፌስ ቡክ ገጽ፡ https://www.facebook.com/sidamabanksc ይጎብኙ ወይም በስልክ ቁጥር 046 212 3591 ወይም 046 220 0850 ይደውሉ፡፡

ሲዳማ ባንክ – የሁሉም ባንክ!