ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክስዮኖች በሙሉ

Overview

 • Category : Announcement
 • Posted Date : 10/29/2022
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 12/03/2022

Description

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም . ባለአክስዮኖች በሙሉ

የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም . ባለአክስዮኖች 5 መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤና 2ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ  ህዳር 24/2015 . ከጠዋቱ 230 በአዲስ አበባ ቂርቆስ ክ/ከተማ በኢሊሊ ኢንተርናሽናል አዳራሽ ስለሚካሄድ ባለ አክስዮኖች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተጠቀሰው ቀን፣ሰዓትና ቦታ በስብሰባው ላይ እንዲገኙ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያቀርባል፡፡  

  የ5ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

 1. የጉባኤውን አጀንዳ ማጽደቅ፤
 2. የጉባኤዉን ድምፅ ቆጣሪዎች እና ፀሀፊ መሰየም፤
 3. የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥ ፤
 4. በተራ ቁጥር 3 ሥር በቀረበዉ ሪፖርት ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፤
 5. የተቋሙን የውጭ እና የዉሰጥ ኦድተር ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥ ፤
 6. በተራ ቁጥር 5 ሥር በቀረበዉ ሪፖርት ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ ፤
 7. የዳይሬክተሮች ቦርድ ወርሃዊ አበልና ዓመታዊ የአገልግሎት ክፍያን መወሰን፤
 8. የዉጪ ኦዲተር መሾምና ክፍያን መወሰን፤
 9. የአክሲዮን ግዥና ዝዉዉርን በማጽደቅና አዳዲስ ባለአክሲዮኖችን መቀበል፤
 10. የመደበኛ ጉባኤዉን ቃለ ጉባኤ ማጽደቅ፡፡

የ2ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

 1. የጉባኤውን አጀንዳ ማጽደቅ
 2. የጉባኤዉን ድምፅ ቆጣሪዎች መምረጥ
 3. የተቋሙን ካፒታል ማሳደግ
 4. የድንገተኛ ጉባኤዉን ቃለ ጉባኤ ማጽደቅ

ማሳሰቢያ፡-

በስብሰባው ላይ መገኘት የማይችል ባለአክሲዮን ከስብሰባው ዕለት ሦስት ቀናት በፊት ማህበሩ ያዘጋጀውን የውክልና መስጫ ሰነድ መካኒሳ ኤስ ሳራ ህንፃ አንደኛ ፎቅ በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ቀርቦ በመፈረም ሌላ ሰው መወከል ይችላል፡፡ ወይንም በውል አዋዋይ የተረጋገጠና በስብሰባው በመካፈል ድምጽ ለመስጠት ግልጽ ስልጣን የሚሰጥ የውክልና ማስረጃ የያዘ ተወካይ በዕለቱ ውክልናውን ይዞ በመቅረብ በስብሰባው ላይ መሳተፍ ይችላል፡፡

ማንኛውም ባለአክሲዮን ለስብሰባው ሲመጣ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያለው መሆኑን የሚያረጋግጥ የታደሰ ቀበሌ መታወቂያ  ወይም  ፓስፖርት ዋናውንና አንድ ኮፒ ይዞ መምጣት ይኖርበታል፡፡

           ሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ!

             የዲሬክተሮች ቦርድ!