ለቢለን ድንበር ተሻጋሪ ደረጃ 1-ሀ የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ባለንብረቶች ማህበር

Overview

  • Category : Announcement
  • Posted Date : 01/11/2023
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 01/17/2023

Description

 ለቢለን ድንበር ተሻጋሪ ደረጃ 1-ሀ የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ባለንብረቶች ማህበር

አባላት በሙሉ የቀረበ ጥሪ

በመንገድ ትራንስፖርት አዋጅ ቁጥር 1274/2014 አንቀጽ 11 ንዑስ ቁጥር 4 እና 5 መሠረት በቀድሞ አዋጅ ተደራጅተውና ተመዝግበው ሲሰሩ የነበሩ የትራንስፖርት ማህበራት ከላይ የተገለፀው አዋጅ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ አግባብነት ባላቸው የአገሪቱ ንግድ ሕጎች መሠረት ወደ ንግድ ማህበርነት የመለወጥና አስፈላጊውን የኦፕሬተርነት የብቃት ማረጋገጫ ሥልጣን ካለው አካል የመውሰድ ግዴታ እንዳለባቸው እና ከተጠቀሰው ጊዜ በኋላ ማንኛውም የትራንስፖርት ማህበር ምዝገባ እንደተሰረዘ ተቆጥሮ ምንም ዓይነት ህጋዊ ሰውነት እንደማይኖረው በግልፅ ተደንግጓል፡፡

በዚህም መሰረት፣ ከላይ በተገለፀው አዋጅ መሠረት የኩባንያው ምስረታውን ሂደት ለማስፈፀም፣ ማህበሩ ራስ ሆቴል በተደረገ የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ላይ መሥራት ኮሚቴ እንደመረጠ ይታወቃል፡፡ መሥራች ኮሚቴውም፣ በህጉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ የኩባንያው ምስረታውን ለማጠናቀቅ ይቻል ዘንድ፣ በተለይም ደግሞ ማንኛውም ዜጋ በመረጠው መንገድ ተደራጅቶ የመሥራት ሕገ መንግስታዊ መብት ከመሆኑም በላይ፣ የትኛውም የንግድ ማህበር ምስረታ ላይ አባላት የሚሰጡት ፈቃድ ከማናቸውም ዓይነት ጉድለት ነፃ እንዲሆን ህጉ የሚያስገድድ መሆኑን መነሻ በማድረግ የምስረታ ላይ ባለው የአክሲዮን ኩባንያ ውስጥ አባል ሆነው የመቀጠል ፍላጐታቸውን እና ፈቃዳቸውን የማህበራችን አባላት እንዲያሳውቁ፤ ከአንድም ሁለት ጊዜ በጽሑፍ እንዲሁም በስልክ ጥሪ ያደረገ ሲሆን፣ ብዛት ያለው የማህበሩ አባልና ባለንብረት የተደረገለትን ጥሪ ተቀብሎ፣ መተማመኛ ሠነድ ላይ በመፈረም ፍቃዳቸውን ሰጥተዋል፡፡ ሆኖም የተወሰኑ የማህበሩ አባላት በተለያየ ምክንያት ጥሪው ሳይደርሳቸው እንዳይቀርና በዋናነትም ጥሪውን በተቻለ አቅም ተደራሽ እንዲሆን ሁሉንም አማራጭ ለመጠቀም መስራች ኮሚቴው ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጥሪውን በዚህ ጋዜጣ ለማድረግ ተገደዋል፡፡

በመሆኑም፣ ይህ የጋዜጣ ጥሪ የመጨረሻ ከዚህ በኋላ በማናቸውም መንገድ ሌላ አዲስ ጥሪ እንደማይደረግና የአክስዮን ምስረታውም በአደራጅ ኮሚቴው ለተደረጉ ጥሪዎች ፈቃዳቸውን በሰጡ የማህበሩ አባላትን ብቻ በማካተት ምስረታው እንደሚከናወንና እንደሚጠናቀቅ ከወዲሁ አውቃቹሁ፤ ውሳኒያችሁን ፣ ይህ የጋዜጣ ጥሪ ከተደረገበት ባሉ አምስት (5) የሥራ ቀናት ውስጥ በማህበሩ ቢሮ በአካል በመቅረብ እንድታሳውቁ እናሳስባለን፡፡

መስራች ኮሚቴው