ለብሔራዊ የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ. ባለአክሲዮኖች በሙሉ

Announcement
NICE-–-National-Insurance-Company-of-Ethiopia-s.c-logo-reportertenders-1

Overview

 • Category : Announcement
 • Posted Date : 10/24/2022
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 11/19/2022

Description

የስብሰባ ጥሪ

ለብሔራዊ የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኩባንያ .. ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ብሔራዊ የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኩባንያ አክሲዮን ማህበር ዋና መ/ቤቱ በቂርቆስ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 04፣ የቤት ቁጥር 894 የሚገኝ እና የንግድ ምዝገባ ቁጥሩ13-1543/87 ሲሆን የማህበሩ ዋና ገንዘብም 250 ሚሊዮን የተፈረመ፣ 180 ሚሊዮን የተከፈለ ነው፡፡

ማህበሩ በኢትዮጵያ ንግድ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 አንቀፅ ከ366 – 372 መሰረት የባለአክሲዮኖችን 29ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እና 15ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ቅዳሜ፣ ህዳር 10 ቀን 2015 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ በሂልተን ሆቴል (Hilton Hotel) የሚያደርግ በመሆኑ ባአለክሲዮኖች በስብሰባው ላይ እንዲገኙ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

29ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

 1. የመደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን አጀንዳዎች ማፅደቅ፤
 2. የተደረጉ የአክስዮን ዝውውሮችን ተቀብሎ ማፅደቅ፤
 3. እ.አ.አ. የ2021/2022 በጀት አመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ የስራ ክንውን ሪፖርትን ማዳመጥ፤
 4. እ.አ.አ. የ2021/2022 በጀት አመት የውጪ ኦዲተሮችን ሪፖርት እና የሂሳብ መግለጫዎችን ማዳመጥ፤
 5. በተራ ቁጥር 2 እና 3 በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ ተወያይቶ መወሰን፤
 6. እ.አ.አ. የ2021/2022 በጀት አመት የተጣራ ትርፍ አደላደል እና አከፋፈልን አስመልክቶ የዳይሬክተሮች ቦርድ ባቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ተወያይቶ መወሰን፤
 7. እ.አ.አ. የ2022/2023 በጀት አመት የውጪ ኦዲተሮች መምረጥ እና የስራ ዋጋቸውን ተወያይቶ መወሰን፤
 8. የዳይሬክተሮች ቦርድ እ.አ.አ. የ2021/2022 በጀት አመት ዓመታዊ ክፍያን እና የ2022/2023 በጀት አመት ወርሃዊ አበል ላይ ተወያይቶ መወሰን፤
 9. የአስመራጭ ኮሚቴ አባላትን ክፍያ መወሰን፤
 10. እ.አ.አ. ለ2023/2024 በጀት አመት ስለሚደረገው የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምርጫ የአስመራጭ ኮሚቴ አባላትን መምረጥ፤
 11. የመደበኛ ጠቅላላ ጉባኤን ቃለጉባኤ ማፅደቅ፡፡

15ኛው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

 1. የአስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤውን አጀንዳዎች ማፅደቅ፤
 2. የኩባንያውን ካፒታል ለማሳደግ በ14ኛው ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ የተላለፈውን የክፍያ ጊዜ ውሳኔ በተመለከተ ተወያይቶ መወሰን፤
 3. የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እ.አ.አ. በሴፕቴምበር 15 ቀን 2022 ባወጣው መመሪያ (Directive Number SIB 57/2022) መሰረት የኩባንያውን የተከፈለ ካፒታል ስለማሳደግ ተወያይቶ መወሰን፤
 4. የኩባንያውን የመመስረቻ ፅሁፍ ስለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ ላይ ተወያይቶ መወሰን፤
 5. የአስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤን ቃለጉባኤ ማፅደቅ፡፡

ማሳሰቢያ፡

 1. በጉባኤው ላይ በአካል መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ተወካይ በመሰየም መሳተፍ ይችላሉ፡፡ ለዚህም ጉባኤው ከሚካሄድበት ቀን ቢያንስ ከ3 የሥራ ቀናት በፊት በኩባንያው ዋና መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 13 (ቦርድ ክፍል) በመቅረብ የተዘጋጀውን የውክልና መስጫ ቅፅ በመፈረም ወይም በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ጠቅላይ ዐ/ሕግ የሰነዶች ምዝገባ እና ማረጋገጫ ፅ/ቤት ተረጋግጦ የተሰጠ የውክልና ስልጣን ማስረጃ ዋናውን እና አንድ ኮፒ በስብሰባው ዕለት ይዞ በመቅረብ መሳተፍ ይቻላል፡፡
 2. ባለአክሲዮኖችም ሆኑ ተወካዮች ወደ ስብሰባው ቦታ ሲመጡ የራሳቸውን የታደሰ መታወቂያ ካርድ ወይም የታደሰ ፓስፖርት ወይም የታደሰ መንጃ ፈቃድ ዋናውን እና ኮፒ ይዘው መቅረብ እንዳለባቸው እናሳስባለን፡፡
 3. ተወካዮች የውጪ ሀገር ዜግነት ያላቸው ከሆኑ ትውልደ ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ እንዲያቀርቡ እንጠይቃልን፡፡

የዳይሬክተሮች ቦርድ