ለብርሃን ባንክ አ.ማ. ባለአክስዮኖች የተላለፈ የጉባኤ ጥሪ
Overview
- Category : Announcement
- Posted Date : 10/15/2022
- Phone Number : 0116185722
- Source : Reporter
- Closing Date : 10/27/2022
Description
የማህበሩ ዋና ገንዘብ/ካፒታል/ 3,168,372,000
የምዝገባ ቁጥር 06/1/28428/01
ለብርሃን ባንክ አ.ማ. ባለአክስዮኖች የተላለፈ የጉባኤ ጥሪ
የብርሃን ባንክ አ.ማ. ባለአክሲዮኖች 13ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ሐሙስ ጥቅምት 17 ቀን 2015 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ፤ ቦሌ በሚገኘው ሚሊኒየም አዳራሽ ይካሔዳል፡፡ ስለሆነም የባንኩ ባለአክሲዮኖች በሙሉ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ ፓስፖርት ወይም መንጃ ፍቃድ በመያዝ በጉባኤው ላይ እንድትገኙ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪ ያቀርባል፡፡
የመደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳ
1, አጀንዳውን ማጽደቅ
2, የተከናወኑ የአክስዮን ዝውውሮችን ማጽደቅና አዳዲስ ባለአክስዮኖችን መቀበል
3, የዳይሬክተሮች ቦርድን እ.ኤ.አ. የ2021/22 ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥ
4, የውጭ ኦዲተሮችን እ.ኤ.አ. የ2021/22 ዓመታዊ የኦዲት ሪፖርት ማዳመጥ
5, ከዚህ በላይ በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ ተወያይቶ መወሰን
6, የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ አባላትን አበል መወሰን
7, የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ አባላትን መምረጥ
8, በዘመኑ የተጣራ ትርፍ አደላደል እና አከፋፈል ላይ ተወያይቶ መወሰን
9, የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ወርኃዊ አበልና ዓመታዊ ክፍያ መወሰን
10,በተጓደሉ የቦርድ አባል ምትክ የተተኩትን ዳይሬክተር ሹመት ማጽደቅ
11,የጉባዔውን ቃለጉባዔ ማጽደቅ የሚሉት ናቸው
ማሳሰቢያ
በጉባኤው ላይ ለመገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ቀጥሎ በተመለከተው መሠረት በወኪሎቻቸው አማካይነት መሳተፍ ይችላሉ
ጉባኤው ከሚካሄድበት ቀን አስቀድሞ ባሉት ቀናት ውስጥ ቦሌ ድልድይ ፊት ለፊት በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት የአክስዮን አስተዳደር ክፍል በመገኘት የውክልና ፎርም/ቅጽ በመሙላት ተወካይ በመወከል ወይም
በስብሰባው ለመገኘትና ድምጽ ለመስጠት የሚያስችል የውክልና ማስረጃ ያለው ተወካይ ዋናውን እና አንድ ፎቶ ኮፒ በጉባኤው ዕለት ይዞ እንዲቀርብ በማድረግ
የብርሃን ባንክ አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ
Follow us
Tel +251 116 18 57 22 / +251 116 18 57 32 / +251 116 63 20 83
Fax +251 11 662 3431 Swift BERHETAA E-mail [email protected] www.berhanbanksc.com P.O.Box 387 Code 1110, Addis Ababa,Ethiopia