ለአዋሽ ባንክ ባለአክሲዮኖች

Awash-Bank-logo-Reportertenders-14

Overview

  • Category : Announcement
  • Posted Date : 11/30/2022
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 11/30/2022

Description

ለአዋሽ ባንክ ባለአክሲዮኖች

ህዳር 20 ቀን 2012 ዓ.ም የባንኩ ካፒታል ወደ 12 ቢሊዮን እንዲያድግ የተወሰነውን የአክሲዮን ክፍያ ላልጨረሱ ባለአክሲዮኖች

ህዳር 20 ቀን 2012 ዓ.ም በተካሄደው 16ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ የባንኩ የተከፈለ ካፒታል ከብር 6 ቢሊዮን ወደ ብር 12 ቢሊዮን እንዲያድግና እስከ ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ተከፍሎ እንዲጠናቀቅ መወሰኑ ይታወሳል፡፡

ሆኖም የባንኩ ባለአክሲዮኖች ህዳር 17 ቀን 2015 ዓ.ም ባካሄዱት 17 አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ከላይ የተገለፀውን የካፒታል ዕድገት ክፍያ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተከፍሎ እንዲጠናቀቅ ተወስኗል፡፡

በመሆኑም ከአሁን ቀደም የተደለደለላችሁን አክሲዮን ክፍያ ያላጠናቀቃችሁ ባለአክሲዮኖች እስከ ታህሳስ 15 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ከፍላችሁ እንድታጠናቅቁ በትህትና እናሳውቃለን፡፡

እስከ ታህሳስ 15 ቀን 2015 ዓ.ም የጊዜ ገደብ ውስጥ ያልተከፈለ አክሲዮን ካለ በአስቸኳይ ጉባኤው በተሰጠው ውሳኔ መሰረት ተጨማሪ አክሲዮን ለመግዛት ተመዝግበው እየተጠባበቁ ለሚገኙ ባለአክሲዮኖች የሚሸጡ መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡ እናመሰግናለን፡፡

አዋሽ ባንክ