ለአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. ባለአክሲዮኖች የሃያ ስድስተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች

Announcement
Awash-Bank-logo-Reportertenders-1

Overview

 • Category : Announcement
 • Posted Date : 11/08/2021
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 11/28/2021

Description

ለአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. ባለአክሲዮኖች

የጉባዔ ጥሪ

 የሃያ   ስድስተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች

የአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. የባለአክሲዮኖች ሃያ ስድስተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ በኢፌዲሪ የንግድ ሕግ አንቀጽ 367፣ 370፣ እና በባንኩ መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 15 መሠረት ቅዳሜ ህዳር 18 ቀን 2014 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ሒልተን ሆቴል ይካሄዳል፡፡ ስለሆነም ባለአክሲዮኖች በአካል ወይም በሕጋዊ ወኪሎቻችሁ አማካይነት በተጠቀሰው ቀንና ቦታ በጉባዔው ላይ እንድትገኙ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ በአክብሮት ይጋብዛል፡፡

 1. እስከ ጉባዔው ቀን ድረስ የተከናወኑትን የአዳዲስ አክሲዮኖች ግዥ፣ ዝውውር እና የባለአክሲዮኖችን ቁጥር /ብዛት/ ማሳወቅ፤
 2. የዳይሬክተሮች ቦርድን እ.ኤ.አ. የ2020/21 ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥና መርምሮ ማፅደቅ፣
 3. የውጭ ኦዲተሮችን እ.ኤ.አ. የ2020/21 ዓመታዊ የሂሳብ ሪፖርት ማዳመጥና መርምሮ ማፅደቅ፤
 4. እ.ኤ.አ ሰኔ 30 ቀን 2021 ዓ.ም ስለተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት ትርፍ አደላደል የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ ማፅደቅ፤
 5. የውጭ ኦዲተሮችን መሾምና ክፍያቸውን መወሰን፣
 6. የዳይሬክተሮች ቦርድን እ.ኤ.አ የ2020/21 የሂሳብ ዓመት ክፍያ መወሰን፤
 7. የዳይሬክተሮች ቦርድ እ.ኤ.አ. የ2021/22 ወርሃዊ አበል ክፍያ መወሰን፣
 8. የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ መምረጥ፤ እንዲሁም ወርሃዊና ዓመታዊ ክፍያቸውን መወሰን፣
 9. የዕለቱን ጉባዔ ቃለ ጉባዔ ማጽደቅ።

ማሳሰቢያ፡-

 1. በጉባዔው ላይ መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ከህዳር 13 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ህዳር 17 ቀን 2014 ዓ.ም 10፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በባንኩ ዋና መ/ቤት ፋይናንስ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት በመገኘት የእንደራሴነት (የውክልና ፎርም/ቅጽ) በመሙላት ወይም ውል ለመዋዋል ሥልጣን በተሰጠው አካል ፊት የተሰጠ በስብሰባ ላይ ለመገኘትና ድምጽ ለመስጠት የሚያስችል የውክልና ሰነድ ዋናውን እና አንድ ቅጂ ይዘው በመምጣት በጉባዔው ላይ መሳተፍ ይችላሉ።
 2. ባለአክሲዮኖችም ሆኑ ወኪሎች ወደ ስብሰባው ቦታ ሲመጡ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፣ ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ መያዝ አለባቸው።
 3. በተጨማሪም የድርጅት ተወካዮች የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ ወይም ተመሳሳይ የሃላፊነት ደረጃ ላይ ያሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ወይም ድርጅቱን ወክለው እንዲገኙ የሚያረጋግጥ የተመዘገበ ቃለ ጉባኤ ወይም በውል አዋዋይ ፊት የተሰጠ የውክልና ሰነድ ይዘው መቅረብ ያለባቸው መሆኑን እናሳውቃለን።
 4. ኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባወጣው መመሪያ በስብሰባ አዳራሾች የመያዝ አቅም ላይ ገደብ የተጣለ በመሆኑ ባለአክሲዮኖች እንዴራሴ/ወኪል እንዲሾሙ የሚመከር ሲሆን በጉባዔው ላይ የሚገኙ ባለአክሲዮኖችም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል (ማስክ) ማድረግ እና ሌሎች የጥንቃቄ እርምጃዎችን መከተል አለባቸው፡፡

ስለባንኩ መረጃ፡- አድራሻ አዲስ አበባ ከተማ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 07፣ ዋና የንግድ ምዝገባ ቁጥር KK/AA/2/0006147/2006፣ የባንክ ሥራ ፍቃድ ቁጥር LBB/001/94፣ ይህ ማስታወቂያ እስከተዘጋጀበት ድረስ የባንኩ የተፈረመ ካፒታል ብር 11,984,737,000፡፡

የአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ

 የዳይሬክተሮች ቦርድ