ለ ቢኤም የቤት ግንባታ እና ኪራይ አክሲዮን ማህበር ባለአክሲዮኖች በሙሉ፤

Overview

 • Category : Announcement
 • Posted Date : 11/22/2022
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 12/18/2022

Description

የስብሰባ ጥሪ ማስታወቂያ፤

ለ ቢኤም የቤት ግንባታ እና ኪራይ አክሲዮን ማህበር ባለአክሲዮኖች በሙሉ፤

የማህበሩ ባለአክሲዮኖች ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ስብሳባ እሁድ ታህሳስ 9 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ በኃይከን ሆቴል ውስጥ ስለሚካሄድ የማህበሩ ባለአክሲዮኖች በተጠቀሰው ቦታ’ቀንና ሰዓት እንድትገኙ የማህበሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ የስብሰባ ጥሪ ያቀርባል፡፡ በአዲሱ የንግድ ህግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 አንቀጽ 370 እና 371 ድንጋጌዎች መሠረት፤-

 1. የማህበሩ ስም፡- ቢ.ኤም የቤት ግንባታ እና ኪራይ አክሲዮን ማህበር
 2. የማህበሩ ዓይነት፡- አክሲዮን ማህበር

iii. የማህበሩ ዋና ገንዘብ፡- ጠቅላላ ብር 129,072,000.00 (አንድ መቶ ሀያ ዘጠኝ ሚሊዮን ሰባ ሁለት ሺ)

 1. ዋና መስሪያ ቤቱ የሚገኝበት ቦታ፡- አ/አበባ ከተማ፤የካ ክ/ከተማ፤ወረዳ 02፤የቤት ቁጥር_ኩርቱ ህንፃ 803
 • የመደበኛ ጠቅላላ ስብሰባ አጀንዳዎች
 1. የ2014 ዓ.ም የበጀት ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ የስራ ክንውን ሪፖርት ማድመጥ እና ተወያይቶ ማፅደቅ፤
 2. ነሐሴ 9 ቀን 2013ዓ.ም እንዲከፈል የተደለደለው ያልተከፈሉ አክሲዮኖች የክፍያ ጊዜያቸው በመጠናቀቁ በአጀንዳው ላይ ውሳኔ መስጠት፤
 3. የማህበሩን የውጭ ባለፈቃድ ኦዲተር ማፅደቅ፤

ማሳሰቢያ፡-

በማህበሩ ባለአክሲዮኖች መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ የሚሳተፉ ባለአክሲዮኖች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ወይም አቻ መታወቂያ እና ስብሳባ ላይ ለመሳተፍ’ድምጽ ለመስጠት እና ውሳኔ ለማሳለፍ የሚያስችል ህጋዊ የውክልና ስልጣን ማረጋገጫ ሰነድ እና የእነዚህኑ ሰነዶች ዋና እና የእንዳንዳቸውን ሰነዶች ኮፒ ይዛችሁ እንድትገኙ እናስታውቃለን፡፡  ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን ህጋዊ የሰነድ ማስረጃዎች አሟልቶ ያልተገኘ ግለሰብ በዕለቱ በሚካሄደው የማህበሩ ባለአክሲዮኖች ጠቅላላ መደበኛ ስብሳባ ላይ መሳተፍ የማይችል መሆኑን በቅድሚያ እናሳውቃለን፡፡

                                                  የ ቢ.ኤም አክሲዮን ማህበር

                                                    የዳይሬክተሮች ቦርድ