ሉተራን የዓለም ፌዴሬሽን ኢትዮጵያ ከቀረጥ ነፃ የገቡና ያገለገሉ 15 ተሸከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ ከሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ባለሥልጣን ጋር በመተባበር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Lutheran-World-Federation-LWF-Ethiopia-logo

Overview

 • Category : Vehicle Sale
 • Posted Date : 11/07/2022
 • Phone Number : 0111580925
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 11/25/2022

Description

ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 01/2022

ሉተራን የዓለም ፌዴሬሽን ኢትዮጵያ ከቀረጥ ነፃ የገቡና ያገለገሉ 15 ተሸከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ ከሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ባለሥልጣን ጋር በመተባበር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ ለሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ከዚህ በታች በተመለከተው የጨረታ መመሪያ መሠረት መሳተፍ ይችላል፡፡

 1. 1. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከሰኞ እስከ አርብ በሥራ ሰዓት የጨረታውን ሰነድ ብር 300.00 /ሦስት መቶ/ በመክፈል ከቢሮ ቁጥር 25 ማግኘት ይችላሉ፡፡
 2. 2. ተጫራቾች ተሸከርካሪዎቹ በሚገኙበት ሳሪስ አቦ ከፍ ብሎ በሚገኘው የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ፤ ግላንስ ትሬዲንግ ሃ/የ/የግል ድርጅት ግቢ ውስጥ በመገኘት በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ መመልከት ይችላሉ፡
 1. 3. ተጫራቾች ለመግዛት የሚፈልጉትን ተሸከርካሪ ዋጋ በጨረታው ሰነድ ሰንጠረዥ ውስጥ በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ላይ በመሙላት በታሸገ ኤንቬሎፕ አድርጎ ለዚሁ ጨረታ ማስገቢያ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 የሥራ ቀናት ውስጥ 5 ኪሎ ሉተራን ዋናው በሮ ማስገባት ይችላሉ፡፡
 2. 4. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት አንድ ተሽከርካሪ 20 በመቶ /20%/ በሉተራን የዓለም ፌዴሬሽን ስም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ /CPO/ ከጨረታ ዋጋ ማቅረቢያው ጋር በማያያዝ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 3. 5. ጨረታው ሕዳር 16 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ተዘግቶ ሕዳር 19 ቀን 2015 ዓ.ም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ላይ መካኒሳ ጀርመን አደባባይ አጠገብ በሚገኘው የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ፤ ጉዲና ቱምሳ ሁለንተናዊ የስልጠና ማዕከል ግቢ ውስጥ ይከፈታል፡፡
 4. 6. የጨረታው አሸናፊ በግልጽ ማስታወቂያ ሠሌዳ ላይ ከተገለጸበት ዕለት ጀምሮ በተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ የሚፈለግበትን ክፍያ በመክፈል ተሽከርካሪውን መረከብ ይኖርበታል፡፡በዚሁ መሠረት የማይፈጽም ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ ያሲያዘው ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ አሸናፊነቱም ይሰረዛል፡፡
 5. በዚህ ጨረታ አሸናፊ የሚሆኑት ተጫራቾች የባለቤትነት ስም ዝውውር ጋር የተያያዙ ክፍያዎችን በመፈጸም ተሸከሪካሪውን ይረከባሉ፡፡
 6. በጨረታው ተሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ /ቦንድ/ የጨረታው አሸናፊዎች የሚፈለግባቸውን ክፍያ እንዳጠናቀቁ የሚመለስላቸው ሲሆን በጨረታው አሸናፊ ለሆኑ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ከቀሪው ክፍያ ጋር ተደምሮ የሚታሰብላቸው ይሆናል፡፡
 7. ተጫራቾች ስለሽያጩ ዝርዝር ሁኔታ ከጨረታው ሰነድ ጋር ከተያያዘው የተጫራቾች መመሪያ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
 8. 10. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መበቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ሉተራን የዓለም ፌዴሬሽን ኢትዮጵያ

አድራሻ፡- 5 ኪሎ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ፊት ለፊት ስልክ: – 011 1580925