ሐምብራ ቢዝነስ ግሩፕ አ.ማ 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤዉን እና 6ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ
Overview
- Category : Announcement
- Posted Date : 12/28/2022
- Source : Reporter
- Closing Date : 01/22/2023
Description
የባለ አክስዮኖች መደበኛ እና ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ
ሐምብራ ቢዝነስ ግሩፕ አ.ማ 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤዉን እና 6ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ እሁድ ጥር 14 ቀን 2015 አ.ማ ከጠዋቱ 2:30 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ (ኮልፌ / አጠና ተራ ) በሚገኘው እፎይታ የገበያ ማዕከል የመሰባሰቢያ አዳራሽ ስለሚካሄድ ፣ ባለአክስዮኖች በአካል ወይም በህጋዊ ወኪሎቻችሁ አማካኝነት በተጠቀሰው ቀን ሰዓትነና ቦታ በጉባዔው ላይ እንድትገኙ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን በአክብሮት ያቀርባል፡፡
የመደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች
- የጉባኤውን አጀንዳዎች ማፅደቅ
- የዳይሬክተሮች ቦርድ የስራ ክንውን ሪፖርት መርምሮ ማፅደቅ
- የገለልተኛ ኦዲት ሪፖርተሮችን መርምሮ ማፅደቅ
- የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት የአገልግሎት ጊዜ ማራዘም
- የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት የሥራ ዋጋ የክፍያ መጠን ማስተካከል
- የስብሰባውን ቃለ ጉባኤ ማፅደቅ ናቸው
የድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች
- የጉባኤውን አጀንዳዎች ማፅደቅ
- የአክሲዩን ዋጋ ትመና መርምሮ ማፅደቅ
- የስብሰባውን ቃለ ጉባኤ ማፅደቅ ናቸው
ማሳሰቢያ ፡ ባለአክስዮኖች በጉባኤው ላይ ለመገኘት
- የማህበሩ አባልነት ዲጂታል መታወቂያ
- የታደሰ መታወቂያ፣ መንጃ ፈቃድ ወይም ፓስፖርት ዋናውን ከኮፒ ጋር ይዘው መገኘት ይኖርባቸዋል
- በሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ወይም አግባብ ባለው አካል በተሰጠው ውክልና በሰብሰባ የሚገኝ ተወካይ የውክልናውን ዋና ከኮፒ ጋር እና የታደሰ መታወቅያ፣ መንጃ ፈቃድ ወይም ፓስፖርት ዋናውን ከኮፒ ጋር ይዘው መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡
- በስብሰባው ላይ ለመገኘት የማይችል ባለአክስዮን ከስብሰባው ዕለት ቢያንስ ሶስት ቀን በፊት አክስዮን ማህበሩ ለዚሁ አላማ ያዘጋጀውን የውክልና መስጫ ቅፅ በማህበሩ ዋና መ/ቤት ድረስ በአካል ተገኝቶ በመፈረም ሌላ ሰው መወከል ይችላል፡፡