ሐበሻ ሲሚንቶ አክሲዮን ማህበር የተለያዩ የደህንነት መጠበቂያ ዕቃዎችን ህጋዊ ፈቃድ ካላቸው ተጫራቾች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

Habesha-Cement-logo

Overview

 • Category : Textile & Leather Products Sell & buy
 • Posted Date : 04/24/2021
 • Phone Number : 0114163273
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 05/10/2021

Description

Procurement bid No. 01/Safety Materials/2021

የተለያዩ የደህንነት መጠበቂያ ዕቃዎች ግዥ ጨረታ ማስታዎቂያ

ሐበሻ ሲሚንቶ አክሲዮን ማህበር የተለያዩ የደህንነት መጠበቂያ ዕቃዎችን ህጋዊ ፈቃድ ካላቸው ተጫራቾች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ተጫራቾች በዝርዝር ለቀረቡት ዕቃዎች  የመሸጫ ዋጋ በፖስታ አሽገው ለሶርሲንግ እና ግዥ መምሪያ እስከ  ግንቦት 02 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በዕለቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት መሆኑን እያሳወቅን ፤ ተወዳዳሪዎች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ከላይ እስከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ድረስ ብቻ ከታች በተመለከተው አድራሻ ማቅረብ የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ማሳሰቢያ

 1. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር የጨረታ ሰነዱ ላይ መመልከት ይችላሉ፡፡
 2. ተጫራቾች በአካል በመቅረብ በሚያስመዘግቡት የኢሜል አድራሻ የጨረታ ሰነድ የሚላክላቸው  ይሆናል፡፡
 3. ተጫራቾች ህጋዊ የሆነ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የፈቃዳቸውን ኮፒ ከመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር አብረው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 4. በጨረታው የሚሳተፍ ማንኛውም ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (ብር አስር ሺህ) በሲፒኦ ማቅረብ አለበት፡፡
 5. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 6. አሸናፊው ተጫራች ዕቃዎቹን በ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
 7. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በቀረበው የዋጋ ማቅረቢያ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡

ኩባንያው የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡ ወንጌላዊት ህንፃ ፊት ለፊት ካስማ ህንፃ 8ኛ ፎቅ ስልክ 0114163273

ሐበሻ ሲሚንቶ አ.ማ