ሐበሻ ሲሚንቶ አ.ማ. የተለያዩ የደህንነት መጠበቂያ መገልገያዎች ለመግዛት የወጣ ጨረታ
Overview
- Category : Security & Protection Equipment Guarding
- Posted Date : 01/18/2023
- Source : Reporter
- Closing Date : 01/24/2023
Description
ሐበሻ ሲሚንቶ አ.ማ.
የተለያዩ የደህንነት መጠበቂያ መገልገያዎች ለመግዛት የወጣ ጨረታ
የተጫራቾች መመሪያ እና ዋጋ ማቅረቢያ
Procurement bid No. 05/ Personal Protective Equipment/2023
- ማንኛውም ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈለ ድርጅት በጨረታው መወዳደር ይችላል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ዋጋ የሚያቀርቡባቸውን እቃዎች መጥቀስ/ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም ዋጋ ያቀረቡበትን የዕቃ አይነት በግልጽ መጻፍ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ዋጋ ላቀረቡበት እቃ ሳምፕል ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን 50 (ሀምሳ ሺህ) ብር በሲፒኦ ወይንም የባንክ ጋራንቲ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ጥር 15 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ በ4፡00 ተዘግቶ በእለቱ 4:30 ከላይ በተመለከተው ዋና መስሪያ ቤት ይከፈታል፡፡
- ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርቡ የጨረታ ሰነዶችም ሆኑ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ የሚደረጉ የማሻሻያ ጥያቄዎች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
- አሸናፊ ሆኖ የተመረጠ ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ውል በመግባት ከ5 ባልበለጡ የስራ ቀናት ውስጥ ዕቃዎቹን ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
- ድርጅቱ ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ጀምሮ በ10ቀናት ጊዜ ውስጥ አሸናፊውን በመለየት ያሳውቃል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከቫት ወይም ከማንኛውም የመንግስት ታክስ በፊት ሆኖ ይህንኑ በግልፅ ማመልከት ይኖርበታል፡፡ ይህ ባልሆነበት እና በግልፅ የማያቀርቡ ተጫራቾች ከጨረታው ሊሰረዙ ይችላሉ፡፡ ስርዝ ድልዝ የዋጋ ማቅረቢያ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- ተጫራቾች ከዚህ የጨረታ ሰነድ የተመለከተውን ዝርዝር ሁኔታ የሚያሟላ የመጫረቻ ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ሐበሻ ሲሚንቶ አ.ማ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡