ሕብረት ባንክ አ.ማ በሞጆ ቅርንጫፍ በኩል ለሰጠው ብድር በመያዣነት የያዘውንና ከዚህ በታች የተመለከተውን የመኖሪያ ቤት በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልፅ ሐራጅ (ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል፡፡

hibret-bank-done-logo-reportertenders

Overview

 • Category : House & Building Foreclosure
 • Posted Date : 10/15/2022
 • Phone Number : 0115573772
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 11/17/2022

Description

    ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ

 ሕብረት ባንክ አ.ማ በሞጆ ቅርንጫፍ በኩል ለሰጠው ብድር በመያዣነት የያዘውንና ከዚህ በታች የተመለከተውን የመኖሪያ ቤት በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልፅ ሐራጅ (ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል፡፡

የቅርንጫፉ ስም የተበዳሪ ስም የአስያዥ ስም ቤቱ የሚገኝበት አድራሻና የቦታዉ ስፋት ካርታ ቁጥር የሐራጅ መነሻ ዋጋ በብር ሐራጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት
 

ሞጆ

 

አቶ ፀጉ አለማየሁ

 

አቶ አለማየሁ አንዳርሳ

ሞጆ ከተማ፣ቀበሌ 01፣የቦታ ስፋት 450 ካ/ሜ፣ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውል ቤት፤  

2689/242/A1-Aa/98

 

1,452,935.00

ኅዳር 08 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት

የሐራጅ ደንቦች፡

 1. ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ በሕብረት ባንክ አ.ማ (Hibret Bank S.C.) ስም የተዘጋጀ የባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡ከባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) ውጭ የሚቀርብ የጨረታ ማስያዣ ተቀባይነት የለውም፡፡
 2. አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15(አስራ አምስት) ቀናት ዉስጥ አጠቃልሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡
 3. በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ተበዳሪዎች እና አስያዦች ብቻ ናቸው፡፡
 4. ተጫራቾች በሐራጅ ለመሳተፍ ሲገኙ መታወቂያ መያዝ ይገባቸዋል፡፡ተጫራቾች የሕግ ሰውነት የተሰጣቸው አካላት ከሆኑ ሕጋዊ ሰውነት ያገኙበትን የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት እንዲሁም ሐራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ሰው ስልጣኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት የፀደቀ የመመስረቻ ጽሑፍ(የመተዳደሪያ ደንብ)፣ቃለ ጉባኤ ወይም የውክልና ሥልጣን ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
 5. የሐራጅ ሽያጩ የሚካሄደው የመያዣ ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ላይ ነው፡፡
 6. የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ይደረጋል፡፡
 7. ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከሕግ አገልግሎት መምሪያ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ ከጨረታው ቀን ሶስት ቀናት አስቀድሞ መጎብኘት ይችላሉ፡፡
 8. የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በህግ የተወሰኑ የታክስና ግብር የስም ማዛወሪያ እንዲሁም የሊዝ ክፍያዎችን ጭምር ገዥ/የጨረታዉ አሸናፊ/ ይከፍላል፡፡
 9. ባንኩ ጨረታውን በማንኛውም ጊዜ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 10. ለተጨማሪ መረጃ፡ ሕግ አገልግሎት መምሪያ: በስልክ ቁጥር 0115 57 37 72/ 0114 70 03 15/ 0114 70 03 41 03/47 ወይም ሞጆ ቅርንጫፍ0221 16 01 62/0221 16 05 48 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡