ሕብረት ባንክ አ/ማ በሞጆ ቅርንጫፍ በኩል ለሰጠው ብድር በመያዣነት የያዘውንና ከዚህ በታች የተመለከተውን የመኖሪያ ቤት በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልጽ ሐራጅ (ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል፡፡
Overview
- Category : House & Building Foreclosure
- Posted Date : 01/30/2023
- Closing Date : 02/27/2023
- Phone Number : 0115573772
- Source : Reporter
Description
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ፤
ሕብረት ባንክ አ/ማ በሞጆ ቅርንጫፍ በኩል ለሰጠው ብድር በመያዣነት የያዘውንና ከዚህ በታች የተመለከተውን የመኖሪያ ቤት በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልጽ ሐራጅ (ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል፡፡
የቅርንጫፍ ስም | የተበዳሪ ስም | የአስያዥ ስም | ቤቱ የሚገኝበት አድራሻና የቦታው ስፋት | የካርታ ቁጥር | የሐራጅ መነሻ ዋጋ በብር | ሐራጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት |
ሞጆ | አቶ ፀጉ አለማየሁ | አቶ አለማየሁ አንዳርሳ | ሞጆ ከተማ፣ቀበሌ 01፣የቦታ ስፋት 450 ካ/ሜ፣ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውል ቤት | 2689/242/A1-Aa/98 | 1,452,935.00 | የካቲት 21 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት |
የሐራጅ ደንቦች
- ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ በሕብረት ባንክ አ/ማ (Hibret Bank S.C) ስም የተዘጋጀ የባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በአስራ አምስት ቀናት ዉስጥ አጠቃልሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡
- በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ተበዳሪዎች እና አስያዦች ብቻ ናቸው፡፡
- ተጫራቾች በሐራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ መታወቂያ መያዝ ይገባቸዋል፡፡ተጫራቾች የሕግ ሰውነት የተሰጣቸው አካላት ከሆኑ ሕጋዊ ሰውነት ያገኙበትን የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት እንዲሁም ሐራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ሰው ስልጣኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት ወይም በሌላ ተመሳሳይ ፅ/ቤት የፀደቀ የመመሥረቻ ጽሑፍ፣የመተዳደሪያ ደንብ፣ቃለ ጉባኤ ወይም የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት፡፡
- የሐራጅ ሽያጩ የሚካሄደው የመያዣው ንብረት በሚገኝበት ቦታ ላይ ነው፡፡
- የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ይደረጋል፡፡
- ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከሕብረት ባንክ ሕግ አገልግሎት መምሪያ(ከቅርንጫፉ) ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ ከጨረታው ቀን ሶስት ቀናት አስቀድሞ መጎብኘት ይችላሉ፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በህግ የተወሰኑ የታክስና ግብር የስም ማዛወሪያ እንዲሁም የሊዝ ክፍያዎችን ጭምር ገዥ(የጨረታው አሸናፊ) ይከፍላል፡፡
- ባንኩ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ የሕግ አገልግሎት መምሪያ በስልክ ቁጥር 0115-57-37-72 /0114-70-03-15/47/41-03 ወይም ሞጆ ቅርንጫፍ 0221-16-01-62/05-48/01-45 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡