ሕብረት ባንክ አ.ማ. በቅርንጫፉ በኩል ለሰጠዉ ብድር በመያዣነት የያዘዉንና ከዚህ በታች የተመለከተውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በግልጽ ሐራጅ (ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል፡፡
Overview
- Category : House & Building Foreclosure
- Posted Date : 12/26/2022
- Phone Number : 0115549718
- Source : Reporter
- Closing Date : 01/28/2023
Description
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ፤
ሕብረት ባንክ አ.ማ. በቅርንጫፉ በኩል ለሰጠዉ ብድር በመያዣነት የያዘዉንና ከዚህ በታች የተመለከተውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በግልጽ ሐራጅ (ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል፡፡
የቅርንጫፍ ስም | የተበዳሪ ስም | የአስያዥ ስም | ቤቱ የሚገኝበት አድራሻና የቦታ ስፋት | የይዞታ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ቁጥር | የሐራጅ መነሻ ዋጋ በብር | ሐራጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት |
አፍሪካ ጎዳና
|
ግሪንላንድ ኃ/የተ/የግ/ማህበር | ቤዛዊት አድማሱ ወንዳፍራሽ | አዲስ አበባ ከተማ፣የካ ክ/ከተማ፣ወረዳ 13 ፣የቦታ ስፋት 290 ካ/ሜ የሆነ ቦታ ላይ የሚገኝ የመኖሪያ ቤት | AA000051305072 | 13,509,320.00 | ጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት |
የሐራጅ ደንቦች
- ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ በሕብረት ባንክ አ.ማ (Hibret Bank S.C.) ስም የተዘጋጀ የባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15(አስራ አምስት) ቀናት ዉስጥ አጠቃልሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል፡፡ በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡
- በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ተበዳሪዎች እና አስያዦች ብቻ ናቸው፡፡
- ተጫራቾች በሐራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ መታወቂያ መያዝ ይገባቸዋል፡፡ተጫራቾች የሕግ ሰውነት የተሰጣቸው አካላት ከሆኑ ሕጋዊ ሰውነት ያገኙበትን የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ሐራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ሰው ስልጣኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት ወይም በሌላ አካል የፀደቀ የመመስረቻ ጽሑፍ(የመተዳደሪያ ደንብ)፣ቃለ ጉባኤ ወይም የውክልና ሰነድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ሐራጁ የሚካሄደዉ በሕብረት ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ሕብር ታወር 26ኛ ፎቅ በሚገኘው የሕግ አገልግሎት መምሪያ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ነው፡፡
- የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ይደረጋል፡፡
- ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከሕግ አገልግሎት መምሪያ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ ከጨረታው ቀን ሶስት ቀናት አስቀድሞ መጎብኘት ይችላሉ፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በህግ የተወሰኑ የታክስና ግብር የስም ማዛወሪያ እንዲሁም የሊዝ ክፍያዎችን ጭምር ገዥ/የጨረታዉ አሸናፊ/ ይከፍላል፡፡
- ባንኩ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፣አፍሪካ ጎዳና ቅርንጫፍ ፡0115 54 97 18/19 ወይም ሕግ አገልግሎት መምሪያ 0114 70 03 15/47 ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡