ሕብረት ባንክ አ/ማ በቅርንጫፉ በኩል ለሰጠዉ ብድር በመያዣነት የያዛቸውን እና ከዚህ በታች የተመለከቱትን ተሽከርካሪዎች በአዋጅ ቁጥር 97/90፣216/92 እና 1147/2011 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልፅ ሐራጅ (ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል፡፡
Overview
- Category : Vehicle Foreclosure
- Posted Date : 01/30/2023
- Closing Date : 02/24/2023
- Phone Number : 0114700315
- Source : Reporter
Description
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ
ሕብረት ባንክ አ/ማ በቅርንጫፉ በኩል ለሰጠዉ ብድር በመያዣነት የያዛቸውን እና ከዚህ በታች የተመለከቱትን ተሽከርካሪዎች በአዋጅ ቁጥር 97/90፣216/92 እና 1147/2011 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልፅ ሐራጅ (ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል፡፡
ተራ ቁጥር | አበዳሪ ቅርንጫፍ | የተበዳሪና አስያዥ ስም | የሰሌዳ ቁጥር | የተሽከርካሪው አይነት | የሻንሲ ቁጥር | የሞተር ቁጥር | የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር( ቫትን ሳይጨምር) | ሐራጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት |
1 |
ፋሲል |
አቶ ሲሳይ ረታ አድገህልኝ | ኢት-03-90323 | ኢቬኮ ጣሊያን ፈሳሽ ጭነት | WJME3TRS40C362705 | F3BEE681G*B220-25 1109* | 5,500,000.00 | የካቲት 16 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 – 4፡00 ሰዓት |
2 | ኢት-03-27910 | ተሳቢ ፈሳሽ ጭነት | EACCBBMEEH0000097 | — | 1,600,000.00 | የካቲት 16 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 – 5፡00 ሰዓት | ||
3 | ኢት-03-90320 | ኢቬኮ ጣሊያን ፈሳሽ ጭነት | WJME3TRS40C362706 | F3BEE681G*B220-25 1156* | 5,300,000.00 | የካቲት 16 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡00 – 6፡00 ሰዓት | ||
4 | ኢት-03-27909 | ተሳቢ ፈሳሽ ጭነት | EACCBBMEEH0000098 | — | 1,500,000.00 | የካቲት 16 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 – 9፡00 ሰዓት | ||
5 | ኢት-03-90457 | ኢቬኮ ጣሊያን ፈሳሽ ጭነት | WJME3TRS40C362707 | F3BEE681G*B220-25 1153* | 5,986,957.00 | የካቲት 16 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 – 10፡00 ሰዓት | ||
6 | ኢት-03-27763 | ተሳቢ ፈሳሽ ጭነት | EACCBBMEEH0000099 | — | 2,734,783.00 | የካቲት 16 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 -11፡00 ሰዓት |
የሐራጅ ደንቦች፡-
- ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ በሕብረት ባንክ አ/ማ (Hibret Bank S.C) ስም የተሰራ የባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊ የሆነ ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል፡፡በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሀራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡
- በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ተበዳሪዎች እና አስያዦች ብቻ ናቸው፡፡ተጫራቾች በሐራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ መታወቂያ መያዝ አለባቸው፡፡ተጫራቾች የሕግ ሰውነት የተሰጣቸው ከሆኑ ሕጋዊ ሰውነት ያገኙበትን የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ሐራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ሰው ስልጣኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ፅ/ቤት ወይም በተመሳሳይ ፅ/ቤት የፀደቀ የመመስረቻ ጽሑፍ (የመተዳደሪያ ደንብ)፣ቃለ ጉባኤ ወይም የውክልና ሰነድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሐራጅ ሽያጩ የሚካሄደው በሕብረት ባንክ አ.ማ ዋና መሥሪያ ቤት ሕንጻ (ሕብር ታወር) 26ኛ ፎቅ ሕግ አገልግሎት መምሪያ ባለው የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ነው፡፡
- የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ይደረጋል፡፡
- ለሐራጅ የቀረቡትን ንብረቶች ለመጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከሕብረት ባንክ አ/ማ ሕግ አገልግሎት መምሪያ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ ከጨረታው ቀን ሶስት ቀናት አስቀድሞ መጎብኘት ይችላል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ (ገዥ)የተጨማሪ እሴት ታክስ የሚከፍል ሆኖ በተጨማሪም ገዢ እንዲከፍላቸው በህግ የተወሰኑ የታክስና ግብር የስም ማዛወሪያ ጭምር ገዥ (የጨረታው አሸናፊ) ይከፍላል፡፡
- ባንኩ ጨረታውን በማንኛውም ጊዜ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ፡ ፋሲል ቅርንጫፍ፡ በስልክ ቁጥር 0581 11 68 70/46 ወይም የሕግ አገልግሎት መምሪያ፡ 0114 70 03 15/47/0115 57 37 72 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡