ሕብረት ባንክ አ.ማ. በአይከል ቅርንጫፍ በኩል ለሰጠዉ ብድር በመያዣነት የያዘዉንና ከዚህ በታች የተመለከተውን የመኖሪያ ቤት በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በግልጽ ሐራጅ (ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል፡፡
Overview
- Category : House & Building Foreclosure
- Posted Date : 01/16/2023
- Phone Number : 00114700315
- Source : Reporter
- Closing Date : 02/17/2023
Description
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ፤
ሕብረት ባንክ አ.ማ. በአይከል ቅርንጫፍ በኩል ለሰጠዉ ብድር በመያዣነት የያዘዉንና ከዚህ በታች የተመለከተውን የመኖሪያ ቤት በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በግልጽ ሐራጅ (ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል፡፡
የቅርንጫፍ ስም | የተበዳሪ ስም | የአስያዥ ስም | ቤቱ የሚገኝበት አድራሻና የቦታዉ ስፋት | የካርታ ቁጥር | የሐራጅ መነሻ ዋጋ በብር | ሐራጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት |
አይከል |
ፈንታሁን አስቻለው መልኬ |
ፈንታሁን አስቻለው መልኬ |
ማዕከላዊ ጎንደር ዞን፣አይከል ከተማ ፣ቀበሌ 01፣የሚገኝና የቦታው ስፋት 200 ካ.ሜ የሆነ የመኖሪያ ቤት |
031368 |
875,575.00 |
የካቲት 09 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት |
የሐራጅ ደንቦች፡-
- ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ በሕብረት ባንክ አ.ማ (Hibret Bank S.C.) ስም የተዘጋጀ የባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በአስራ አምስት ቀናት ዉስጥ አጠቃልሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል፡፡በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፡፡
- በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ተበዳሪዎች እና አስያዦች ብቻ ናቸው፡፡
- ተጫራቾች በሐራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ መታወቂያ መያዝ ይገባቸዋል፡፡ተጫራቾች የሕግ ሰውነት የተሰጣቸው አካላት ከሆኑ ሕጋዊ ሰውነት ያገኙበትን የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ሐራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ሰው ስልጣኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት ወይም በሌላ አካል የፀደቀ የመመስረቻ ጽሑፍ(የመተዳደሪያ ደንብ)፣ቃለ ጉባኤ ወይም የውክልና ሰነድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ሐራጁ የሚካሄደዉ የመያዣው ንብረት በሚገኝበት ቦታ ላይ ነዉ፡፡
- የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ይደረጋል፡፡
- ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከሕግ አገልግሎት መምሪያ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ ከጨረታው ቀን ሶስት ቀናት አስቀድሞ መጎብኘት ይችላሉ፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በህግ የተወሰኑ የታክስና ግብር የስም ማዛወሪያ እንዲሁም የሊዝ ክፍያዎችን ጭምር ገዥ(የጨረታዉ አሸናፊ) ይከፍላል፡፡
- ባንኩ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር አይከል ቅርንጫፍ ፡0583 33 14 39፣ 0583 33 17 53 ወይም ሕግ አገልግሎት መምሪያ 0114 70 03 15/47 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡`