ሕብረት ባንክ አ.ማ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች እና የጥበቃ ቤት በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

hibret-bank-done-logo-reportertenders-1

Overview

 • Category : Other Sale
 • Posted Date : 08/06/2022
 • Phone Number : 0114169757
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 08/16/2022

Description

የሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 008/2014

ሕብረት ባንክ አ.ማ በ 2022/23 የበጀት ዓመት ነባር የባንኩ ቅርንጫፎችን የሪብራንዲንግ ስራ ለማከናወን ዕቅድ የያዘ ሲሆን የኮንስትራክሽን ስራዎችን አፍርሶ ለመውሰድ እንዲያስችል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ማለትም ካውንተሮች፣ አሉሙኒየም ፓርቲሽኖች ፣ስትሮንግ ሩም ብረቶች እና የጥበቃ ቤት በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም አካል ዕቃዎችን አዲስ አበባና አካባቢው ላይ 29 /ሃያ ዘጠኝ/ ቅርንጫፎች እንዲሁም ከአዲስ አበባ ውጭ በልዩ ልዩ ክልሎች 44/አርባ አራት/አጠቃላይ 79/ስባ ዘጠኝ/ ቅርንጫፎች  ከ ሰኞ ነሃሴ 2 ቀን 2014 እስከ ነሃሴ 10 ቀን 2014 ዓ.ም ባሉት 9(ዘጠኝ) ተከታታይ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30-5፡30 እንዲሁም ከሠዓት 7፡30-10፡00 መጫረት የሚቻል መሆኑን እየገለፅን ዝርዝር የንብረቶቹን አይነት ከዚህ በታች ተገልፅዋል፡፡

ተ.ቁ የንብረቶቹ ዝርዝር መለኪያ አዲስ አበባ እና አካባቢው ከአዲስ አበባ ውጪ ምርመራ
1 ካውንተር ML 232 352  
2 አልሙኒየም ፓርቲሽን M2 812 1232  
3 የስትሮንግ ሩም ብረት M2 29 44  
4 የጥበቃ ቤት M2 174 264  

 

 • የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% ሲፒኦ ማስያዝ የኖርባቸዋል፡፡
 • ጨረታው የሚጠናቀቀው ነሃሴ 10 ቀን 2014 ዓ.ም ከሰአት 9፡00 ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በዚሁ ቀን ነሃሴ 10 ቀን 2014 ዓ.ም ከሰአት 9፡30 በንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል ይሆናል፡፡
 • ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ተ.እ.ታን የሚያካትት መሆን አለመሆኑን/ ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
 • ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የጨረታ ዋጋ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ሰንጋ ተራ በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት 4ኛ ፎቅ ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል ማስገባት ይችላሉ፡፡
 • አሸናፊ የሚሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ገንዘብ በ3 (ሶስት) ቀናት ውስጥ ከፍሎ በቀጣይ በሚወጣው ፕሮግራም መሰረት ንብረቶቹን ማንሳት ይኖርበታል፡፡
 • ባንኩ ንብረቶቹን ለመሸጥ የተሻለ መንግድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉበሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 • ለበለጠ ማብራሪያ ሕብረት ባንክ ዋና መ/ቤት ስ.ቁ. +251114-16-97-57 ላይ ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
 • የቅርንጫፎቹን ስም ዝርዝር ሰንጋ ተራ በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ 4ተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል በመምጣት መውሰድ ይቻላል፡፡
 • ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከባንኩ በሚሰጠው የመወዳደርያ (የመጫረቻ ሰነድ)ላይ በተገለፀው ዝርዝር የንብረት አይነቶች መሰረት የሚያስገቡት ዋጋ በነጠላ ዋጋ መግለፅ ይኖርባቸዋል

ሕብረት ባንክ