ሕብር ስኳር አክስዮን ማህበር የሒሳብ ምርመራ (ኦዲት ስራ) ጨረታ ማስታወቂያ

Overview

 • Category : Auditing Related
 • Posted Date : 01/11/2021
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 01/27/2021

Description

የሒሳብ ምርመራ (ኦዲት ስራ) ጨረታ ማስታወቂያ

ሕብር ስኳር አክስዮን ማህበር ከ2013 – 2015 በጀት አመት ለ 3 አመት የሚቆይ የሂሳብ ምርመራ (ኦዲት) ስራ በተፈቀደለትና በተመሰከረለት የውጭ ኦዲተር የሂሳብ መዝገብ ለማስፈተሸና ለማስመርመር (ኦዲት ለማስደረግ) ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያàሉ ኦዲተሮች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡

ተወዳዳሪዎች ማàላት ያለባቸው መስፈርቶች፡-

 • የዘመኑን የ2012 በጀት አመት ግብር ስለመክፈሉ የግብር ክፍያ ምስክር ወረቀት (ክሊራንስ) ማቅረብ የሚችል¿
 • ለ2013 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል¿
 • በሚመለከተው ተÌም የተሰጠ የሞያ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል¿
 • የታክስ መለያ ቁጥር ( TIN No) ያለው/ት/
 • የተ.እ.ታ. ተመዝጋቢ የሆነ/ች/
 • ተወዳዳሪዎች ለአገልግሎቱ የሚያስከፍሉት ዋጋ በዝርዝር /Proposale/ እና
 • ሥራውን ሰርቶ የሚያጠናቀቅበትን ጊዜ ማለትም የሂሳብ ምርመራውን አጠናቆ ዘገባውን (Riport) የሚያስረክበት ጊዜ በመግለጽ½
 • ተወዳዳሪዎች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉ 10  ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ መሰረት ሰነዶቹን በታሸገ ኤንቨሎፕ በሥራ ሰዓት እንዲያቀርቡ እንጋብዛለን፡፡
 • ማሳሰቢያ፡- አክስዮን ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 • አድራሻ፡- ከመካኒሳ (ጀሞ) ሚካኤል አደባባይ ወደ ጀሞ ኮንደሚኒየም በሚወስደው መንገድ መቶ ሜትር ያህል አለፍ ብሎ በስተ-ቀኝ በሚገኘው  አፍሪካ ህንፃ 3ኛ ፎቅ ላይ የማህበሩ ዋና መ/ቤት ቢሮ ቁ. 316 እና 317 ማቅረብ ይችላሉ፡፡

የሕብር ስኳር አ.ማ የዲሬክተሮች ቦርድ

Send me an email when this category has been updated