ሕዳሴ ቴሌኮም አክሲዮን ማህበር የውጪ ኦዲተር አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

Hidasei-Telecom-s.c-logo

Overview

 • Category : Auditing Related
 • Posted Date : 09/29/2022
 • Phone Number : 0114653711
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 10/18/2022

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

 ሕዳሴ ቴሌኮም አ.ማ

ጨረታ ቁጥር LT/HT/HO/06/2022

 • ሕዳሴ ቴሌኮም አክሲዮን ማህበር የውጪ ኦዲተር አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
 1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን መስከረም 19 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 8 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡00 – 6፡00 እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከ7፡30 – 10፡00 ድረስ  “ሕዳሴ ቴሌኮም አ.ማ” ደብረዘይት መንገድ ጠብመንጃ ያዥ ባንክ ፊት ለፊት ከበእምነት ምግብ ቤት ጎን በሚገኘው ቤተሳይዳ ሕንጻ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 306 በመቅረብ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ/ በመክፈል እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የታክስ ክሊራንስ ሰርተፍኬት፣ እና የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በመያዝ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
 • ተጫራቾች የሚያቀርቡት
 • አንድ ዋና /Original/ የጨረታ ሰነድ ለብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ ታሽጐ
 • አንድ ቅጂ /Copy/ የጨረታ ሰነድ ለየብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ ታሽጐ እንዲሁም፣
 • ሁሉም በአንድ ላይ በትልቅ ፖስታ ውስጥ ተካቶ በሰም የታሸገ መሆን አለበት፡፡
 • በዋናውና በቅጂው መካከል ልዩነት ቢፈጠር ዋናው ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡ ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡ የተሰረዘ ሰነድ በፊርማ መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡
  • ተጫራቾች የውጪ ኦዲተር አገልግሎት የሚያቀርቡበትን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 10,000.00 /አስር ሺ ብር/ የባንክ ክፍያ ማዘዣ /C.P.O/ ለሕዳሴ ቴሌኮም አ.ማ በሚል ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ቀን ጥቅምት 8 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 306 ሲሆን፣ ጨረታውን የሚከፈትበት ቀን ጥቅምት 8 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 306 ይሆናል::
  • ከላይ የተገለጸውን መመሪያ ባልተከተሉ ተጫራቾች ላይ ወዲያውኑ ጨረታው የሚሠረዝ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  • ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0114-653711 ፋክስ ቁጥር 0114-663649 መጠቀም ይችላሉ፡፡
 • ሕዳሴ ቴሌኮም አ.ማ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ሕዳሴ ቴሌኮም አክሲዮን ማህበር