መስሪያ ቤታችን የተሸከርካሪ መለዋወጫዎች፣ ጎማዎችና ባትሪዎች እንዲሁም የፅህፈት መሣሪያዎችና የፅዳት እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

national-intelligence-and-security-service-logo

Overview

 • Category : Tyre & Battery
 • Posted Date : 07/13/2021
 • Phone Number : 0111238488
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 08/04/2021

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

መስሪያ ቤታችን ለ2014 በጀት ዓመት የተሸከርካሪ መለዋወጫዎች፣ ጎማዎችና ባትሪዎች እንዲሁም የፅህፈት መሣሪያዎችና የፅዳት እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ከዚህ በታች በተገለፀው መሰረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

 1. ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ ያላቸውና የ2013 ዓ.ም ግብር የከፈሉ እንዲሁም በመንግስት ዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆናቸውን፣ ለተጨማሪ እሴት ታክስ መመዝገባቸውንና ጨረታ ለመካፈል የተፈቀደላቸው መሆኑን የሚገልፅ ክሊራንስ ቀኑ ከጨረታ መክፈቻ በፊት የወጣ ማቅረብ የሚችሉ፤
 2. ተጫራቾች ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የሥራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ቀበና ሼል ወረድ ብሎ አደባባዩ ፊት ለፊት ከሚገኘው ቢሮአችን ቀርበው የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
 3. ማንኛውም ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረ (CPO) ከጨረታው መክፈቻ እለት አስቀድሞ ማስያዝ አለባቸው፡፡
 4. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ከላይ በተገለፀው አድራሻ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ፡-
 • የተሸከርካሪ መለዋወጫዎች ሐምሌ 28 ቀን 2013 ዓ.ም
 • የፅህፈት መሣሪያዎችና የፅዳት እቃዎች ሐምሌ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ2፡30 እስከ ከቀኑ 8፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ በዚሁ ዕለት የጨረታው ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 8፡30 ይከፈታል፡፡
 1. ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ዕቃዎች ናሙናዎችን ከተከፈተበት ቀን ማግስት ጀምሮ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ አጠናቀው ማቅረብ አለባቸው፡፡
 2. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርት በ10 ቀን ግዜ ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡
 3. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-

 0111-23-84-88፣ 0111-23-98-24፣ 0111-23-84-64 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 በብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት

የሎጂስቲክስና ኮንስትራክሽን ዋና መምሪያ

Send me an email when this category has been updated