መቅድም ኢትዮጵያ ናሽናል አሶሴሽ ለቢሮ አገልግሎት የሚሆኑ ዕቃዎችና አገልግሎቶች አቅራቢዎችን በማወዳደርና ለ3 ዓመታት ውል በመግባት በቋሚነት አገልግሎቱን መጠቀም ይፈልጋል፡፡

mekdim-ethiopia-national-association-logo

Overview

 • Category : Stationery Supplies
 • Posted Date : 04/23/2021
 • Phone Number : 0111228843
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 05/04/2021

Description

መቅድም ኢትዮጵያ ናሽናል አሶሴሽን

ማስታወቂያ ለዕቃ እና አገልግሎት አቅራቢዎች

(2013-2015 ዓ.ም)

መቅድም ኢትዮጵያ ናሽናል አሶሴሽን ሀገር በቀል የሲቪል ተቋም ሲሆን ድርጅቱ ለተለያዩ ፕጀክቶች ማስፈጸሚያና ለቢሮ አገልግሎት የሚሆኑ ዕቃዎችና አገልግሎቶች አቅራቢዎችን በማወዳደርና ለ3 ዓመታት ውል በመግባት በቋሚነት አገልግሎቱን መጠቀም ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረትም ከታች በዓይነት የተዘረዘሩትን ዕቃዎች እና አገልግሎቶች ለማቅረብ አቅሙና ፍላጎቱ ያላቸው እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

ድርጅታችን በቋሚነት የሚፈልጋቸው የዕቃ/አገልግሎት ዓይነቶች፡-

 1. መድኃኒቶችና የህክምና ዕቃዎች (Pharmaceutical Supplies)
 2. የምግብና ምግብ ነክ ዕቃዎች (Food Items- pasta, Macaroni, edible oil…)
 3. የጽዳት ዕቃዎች (Sanitation goods)
 4. የቢሮ እቃዎች (Office furniture)
 5. የኮምፒውተር ዕቃዎች (Computers & accessories)
 6. የጽሕፈት መሳሪያዎች (Stationaries)
 7. የተሸከርካሪ ጥገና (Vehicle maintenance and service)
 8. የህትመት አገልግሎት (Publishing and Branding)
 9. የተሸከርካሪ መለዋወጫ አቅርቦት (Spare parts)
 10. የደንብና የስራ ልብሶች ስፌት (Uniforms)
 11. የሞባይል ካርድ (mobile card supply)
 12. የሆቴል እና ስብሳባ አዳራሽ (hotel, hall and accommodation)
 13. የማማከር አገልግሎት (consultancy services)
 14. የጄነሬተር ጥገና (generator Maintenance)
 15. የላብራቶሪ ዕቃዎች ጥገና (maintenance of laboratory Equipment)
 16. የኢንሹራንስ ድለላ (insurance brokage service)
 17. የህግ አገልግሎት (legal service)

ስለሆነም ከላይ ከተዘሩት በአንዱ/ፈቃድ ባለው/ መወዳደር የሚፈልግ የ2013 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ሠርቲፊኬትና የቫት ሠርቲፊኬት ፤ የአቅራቢነት ምዝገባ (እንደ አስፈላጊነቱ) ቅጅ በመያዝ አዲስ አበባ ፤ ቀበና ሳንድፎርድ (እንግሊዝ) ትምህርት ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው የመቅድም ኢትዮጵያ ናሽናል አሶሴሽን ዋና መስሪያ ቤት ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 7 (ሰባት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በአካል ወይም በፖስታ ሳ.ቁ 31218 አ.አ ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፤ ለጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 1 22 88 43 መደወል ይቻላል፡፡

ዝርዝር የጨረታ ሰነድ አስፈላጊውን ህጋዊ መስፈርት አማልተው ለተለዩ ብቻ በድርጅቱ ይቀርባል፡፡ ድርጅቱ የተሻለ መንግድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡ እንዲሁም ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡