መከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የህፃናትና ወጣቶች ትያትር ማዕከል ግንባታ ፕሮጀክት(ፕሮ.12-04B) “የውጭ ህንፃ መስታወት የማፅዳት ስራ” በዘርፉ ፍቃድ ባላቸው አካላት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

Defence-Construction-Enterprise-3

Overview

  • Category : Construction Service & Maintenance
  • Posted Date : 10/15/2022
  • Phone Number : 0911815953
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 10/22/2022

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በድርጅታችን መከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የህፃናትና ወጣቶች ትያትር ማዕከል ግንባታ ፕሮጀክት(ፕሮ.12-04B) “የውጭ ህንፃ መስታወት የማፅዳት ስራ”  በዘርፉ ፍቃድ ባላቸው አካላት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 200(ሁለት መቶ ብር) ብቻ ከፍላችሁ ከፕሮጀክት አስተዳደርና ፋይናንስ ክፍል በመውሰድ የምትወዳደሩበትን የመገልገያ እና የእጅ ዋጋ ብቻ ሞልታችሁ በፖስታ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 6(ስድስት) የስራ ቀናት  የግዥ አቅርቦት ቡድን ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባችሁ፡፡ ጨረታው ጥቅምት 12/2015 ዓ/ም ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት 4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡

ተጫራቾች

1.የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፍኬትና ከግብር  ሰብሳቢ ባለስልጣን ጨረታ ለመሳተፍ የተሰጠ ማስረጃ(tax clearance) ማቅረብ አለባቸው፤

2.ከዚህ በፊት ተመሳሳይ ሥራ የሰሩበት ማስረጃ ሰነዶች ማቅረብ እና የሰሩትን ስራ ማሳየት መቻል አለባቸው

3.የሕጋዊ ዶክመንት እና ፋይናንሻል ሰነድ ለየብቻው ታሽጎ መቅረብ አለበት

4.ዝርዝር ሥራው ከጨረታ ሰነዱ በሚገባ መረዳት አለባቸው ሲሆን የተቀመጠው የሥራ መጠን ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡

5.የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ መክፈያ (CPO)ብር 5,000.00 ማስያዝ አለባቸው

6.የህጋዊነ እና ቴክኒካል ሰነዶች ብቻ በጨረታው መክፈቻ ቀን ይከፈታሉ

7.የሞሉትን መወዳደሪያ ዋጋ ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ መግለጽ አለባቸው

8.ፕሮጀክቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

         አድራሻ፡- ፊላሚንጎ ኤግዚቢሽን ማዕከል ጀርባ

                 በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ

                የህፃናትና ወጣቶች ትያትር ማዕከል ግንባታ ፕሮጀክት(ፕሮ.12-04B)

                ስልክ ቁጥር፤09-11-81-59-53