መከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ Deformed reinforcement bar በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

-ኮንስትራክሽን-ዲዛይን-ድርጅት-Logo-1

Overview

 • Category : Aluminum Related Products Supply & Sale
 • Posted Date : 01/02/2021
 • Phone Number : 0114403434
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 01/30/2021

Description

ቀን፡- 21/04/2013 ዓ/ም

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን መከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በባ/ዳር ዙሪያ ሮቢት ባታ ቀበሌ ለሚገነባው ወታደራዊ አካዳሚ ግንባታ ፕሮጀክት (18-06B) ለግንባታ ስራ አገልግሎት የሚውሉ Deformed reinforcement bar ø8 ብዛት 108,569.66 ኪ/ግ፤ ø10 ብዛት 16,659 ኪ/ግ፣ ø12 ብዛት 72,087.84 ኪ/ግ፤ ø14 ብዛት 58,297.80 ኪ/ግ፣ ø16 ብዛት 91,482 ኪ/ግ እና ø20 ብዛት 55,575 ኪ/ግ በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ 

ስለሆነም ፡-ተጫራቾች ማሟላት የሚጠበቅባቸዉ

 1. 1. ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን እና በማንኛውም ጨረታ ለመሳተፍ የሚችሉ መሆኑን የሚገልፅ የታክስ ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
 2. 2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ CPO ዋስትና የሚያቀርቡት ገንዘብ በተጫራቾች መመሪያ ተራ ቁጥር 7.3 እና 7.4 በተጠቀሠው መሠረት በድርጅታችን መከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ስም መሆን አለበት፡፡
 3. 3. ተጫራቾች የጨረታ መመሪያ ሠነዱን እስከ ጥር 8 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ባህር ዳር አካባቢ የምትገኙ ተጫራቾች ዘወትር በስራ ስዓት ቅዳሜን ጨምሮ ፕሮጀክቱ በሚገኝበት ቢሮ ቁጥር 7 መውሠድ የምትችሉ ሲሆን አዲስ አበባ አካባቢ የምትገኙ ተጫራቾች ደግሞ ዘወትር በስራ ሠዓት ወሎ ሠፈር አካባቢ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋናው መስሪያ ቤት የግዥ የሥራ ሂደት ኬዝ ቲም ቢሮ መግዛት ትችላላችሁ፡፡
 4. 4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ፖስታ እስከ ጥር 8 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በባህር ዳር ከተማ አርሚ ፋውንዴሽን ፕሮጀክት (18-05B) ድረስ ለጨረታዉ በተዘጋጀዉ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይችላሉ ፡፡
 5. 5. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የዋጋ ማቅረቢያ ሠነድ ዉስጥ ቀን፣ ፊርማ፣ የድርጅቱ ማህተም ያረፈበትና ሙሉ አድራሻቸውን መግለፅ አለባቸዉ፡፡ ይህ ካልሆነ ሠነዱ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
 6. 6. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ከነቫቱ ወይም ከቫት በፊት ብለው መጥቀስ አለባቸው ካልተጠቀሠ ግን የቀረበው ዋጋ ከነቫቱ ተብሎ ይወሠዳል፡፡
 7. 7. ተጫራቾች የጨረታ ሠነድ ሊገዙ ሲቀርቡ በተፈለገዉ አቅርቦት ዘርፍ የተሠማሩ መሆናቸዉን የሚገልፅ የንግድ ፈቃድ ኮፒ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 8. 8. ጨረታዉ ጥር 8 ቀን 2013 ዓ.ም በባህር ዳር ከተማ አርሚ ፋውንዴሽን (18-05B) ፕሮጀክት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው እለት እና በዚሁ ቦታ ጥር 8 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15 ላይ ይከፈታል ፡፡
 9. 9. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ ፡፡

          አድራሻ፡- መከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ

ባህር ዳር አርሚ ፋውንዴሽን ፕሮጀክት /18-05B/

ከዋናው አስፓልት 500 ኪ.ሜ ገባ ብሎ ከመከላከያ አፓርታማ ጀርባ

ስልክ ቁጥር 058 820 98 63 ይደውሉ

እና

አድራሻ፡- መከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ

የቀጥታ ስልክ ቁጥር 0114-40-34-34/33

ማዞሪያ 0114-42-22-70/71/72

ፖ.ሳ.ቁ. 3414 ፋክስ ቁ.0174-40-04-71/0114-42-07-46

ወሎ ሰፈር የቀድሞው ኖሬላ ግቢ

ድህረ ገፅ፡- www.dce.et,com

ኢሜል፡- INFO @ dec.et.com

ፕሮጀክቱ

Send me an email when this category has been updated