ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃ.የተ.የግል ማህበር ያገለገሉ ብረታ ብረት፣ጎማዎችና የተለያዩ ዕቃዎች ሽያጭ ጨረታ

midroc-Logo-reportertenders

Overview

 • Category : Disposal Sale
 • Posted Date : 07/30/2022
 • Phone Number : 0911561970
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 08/23/2022

Description

 MIDROC GOLD Mine PLC

ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃ.የተ.የግል ማህበር

ያገለገሉ ብረታ ብረት፣ጎማዎችና የተለያዩ ዕቃዎች ሽያጭ ጨረታ

 1. ተጫራቾች በጥቅል አንድ ተብሎ የተመዘገበውን በኩባንያው ዋና መ/ቤት በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በኦዶ ሻኪሶ ለገደንቢ የወርቅ ማዕድን ክልል ውስጥ እንዲሁም በጥቅል ሁለት ተብሎ የተመዘገበው በኩባንያው አዲስ አበባ ጽ/ቤት በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ መንገድ ትራንስፖርት ማስልጠኛ ወደ ሐና ማሪያም አቅጣጫ 500 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው የድርጅቱ መጋዘን በአካል ቀርቦ ለጨረታ የቀረቡትን ያገለገሉ ዕቃዎችን በማየት በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ለጥቅል አንድና ለጥቅል ሁለት ለእያንዳንዳቸው ብር 5000፡-(አምስት ሺ ብር) በማስያዝ እስከ ነሐሴ 16 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መመዝገብ ይቻላል፡፡
 2. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ለጥቅል አንድ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) እንዲሁም ለጥቅል ሁለት ብር 500፡-(አምስት መቶ ብር) በመክፈል የሚፈልጓቸውን ዕቃዎች በመጥቀስ የጨረታ ሰነዱን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ከነሐሴ 02 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ነሐሴ 16 ቀን 2014 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ ከ3፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይችላሉ ጨረታው ነሐሴ 17 ቀን 2014 ዓ.ም በ8ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሁለቱም ቦታዎች ላይ ይከፈታል፡፡
 3. አንድ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የማይችል ሲሆን ነገር ግን አንድ ተጫራች ለሁለቱም ጥቅል መወዳደር ይችላል፡፡
 4. በጨረታው ለወደቁ ተወዳዳሪዎች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ወዲያው ሲመለስላቸው ለአሸናፊዎች ግን ከግዥው ክፍያ ታሳቢ ይሆናል፡፡
 5. የጨረታ አሸናፊው ለሚገዛቸው ያገለገሉ ዕቃዎች የመንግሥት ታክስም ሆነ ተዛማጅ ወጪዎች ሙሉ በሙሉ ይሸፍናል፡፡
 6. የጨረታ አሸነፊዎች ያሸነፉበትን ያገለገሉ ዕቃዎች በሰባት/7/ የሥራ ቀናት ውስጥ ማንሳት አለባቸው ይህ ሳይሆን ቢቀር ያስያዙትን ገንዘብ ሲ.ፒ.ኦ ለድርጅቲ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፡፡
 7. ድርጅቱ የጨረታ ሰነድን ለጥቅል አንድ በዋናው መሥሪያ ቤት ለገደንቢ (ከለቻ) እንዲሁም ለጥቅል አንድና ለጥቅል ሁለት በኩባንያው ቅ/ጽ/ቤት ሰሚት የሞሐ ለስላሳ ፋብሪካ አጠገብ በሚገኘው ፋርማኪዩር ቢሮ ውስጥ ማግኘት ይቻላል፡፡
 8. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ፡- ለበለጠ ማብራሪያ ለጥቅል አንድ ለተጠቀሱት 0911561970 እንዲሁም ለጥቅል አንድና ሁለት 0911547276፣0917833206፣0911852168 ይጠቀሙ፡፡