ማይ ዊሽ ኢንተርፕራይዝ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከዚህ በታች የተገለፁትን ያገለገሉ የTelescopic Handler እና Scaffolder ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Overview

 • Category : Purchases
 • Posted Date : 08/15/2022
 • Phone Number : 0911318856
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 08/20/2022

Description

የBobcat Telescopic Handler እና Scaffolder ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ

ማይ ዊሽ ኢንተርፕራይዝ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከዚህ በታች የተገለፁትን ያገለገሉ የTelescopic Handler እና Scaffolder ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

 1. የእቃው አይነት፡ Telescopic Handler
ሞዴል ክብደትና አቅም የሞተር አይነትና ጉልበት የስሪት አገርና ዘመን የሰራው ሰአት ታርጋ ቁጥር የጨረታ መነሻ ዋጋ ብዛት
Bobcat-T35130S 8.7 እና 3.5 ቶን Perkins/1104D-44TA/

100 የፈረስ ጉልበት

ፈረንሳይ/2015 እ.ኤ.አ 237 ሰአት ስከ-LD-2334 4,000,000.00 01
 1. የእቃው አይነት፡ Villalta Scaffolding with Pins

የስሪት አገርና ዘመን፡ ጣልያን/2020 እ.ኤ.አ. /

The Villalta pin scaffolding consists of a symmetrical portal frame with 6 pins entirely made of S235JRH steel. The following wide range of accessories is included፡

 • Galzanized metal decks (working platform)
 • Galzanized metal decks with hatches/doors
 • Anchor tube with hook
 • Ladder
 • Pressed Right angle couplers four, 4, bolts
 • Horizontal/Diagonal Bracing and tie bar
 • Aadjustable bases

All scaffoldings are painted and hot dip galvanized.

ብዛት: 250 Set ከነአክሰሰሪዎቹ

የጨረታ መነሻ ዋጋ: 10,000.00

 1. የተጫራቾች መመሪያ

በጨረታው መካፈል የሚፈልጉና የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ህጋዊ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች በጨረታው መሳተፈው ይችላሉ፡፡

 1. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ እስከ ነሃሴ 14 ቀን 2014 ዓ.ም. ከረፋዱ 4፡30 ሰአት ድረስ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛትና እቃዎቹን መመልከት ይችላሉ፡፡
 2. ተጫራቾች መጫረት ለሚፈልጉት እያንዳንዱ እቃ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 10% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) በማይ ዊሽ ኢንተርፕራይዝ ስም በማሰራት፤ የሚገዙበትን ዋጋ (ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ) በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ውስጥ በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ ነሃሴ 14 ቀን 2014 ዓ.ም. ከረፋዱ 4፡30 ሰአት ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ በሚቀርበው የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ  ካለ ለውድድር አይቀርብም፡፡
 3. ጨረታው ነሃሴ 14 ቀን 2014 ዓ.ም. ከረፋዱ 4፡30 ሰአት ላይ ተዘግቶ በእለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮቻቸው በተገኙበት ከቀኑ በ5፡00 ሰአት ላይ በድርጅቱ ዋና መ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ይከፈታል፡፡
 4. ከፍተኛ ዋጋ ላቀረበ ተጫራች ድርጅቱ ዋጋውን የሚቀበል መሆን አለመሆኑን በእለቱ ወይም የካቲት 26 ቀን 2014 ዓ.ም.ያሳውቃል፡፡ የጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራች የአሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 (አምስት) የስራ ቀናት ውስጥ የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ ለድርጅቱ ገቢ በማድረግ ንብረቱን መረከብ ይኖርበታል፡፡ ከላይ በተጠቀሰው ግዜ ውስጥ ገቢ ለማያደርግ ተጫራች ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይደረጋል፡፡
 5. ከስም ዝውውር እና እቃዎችን ከማጔጔዝ ጋር የተያያዙ ወጪዎችን አሸናፊው ይሸፍናል፡፡
 6. በጨረታው ላላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት የባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) ወዲያውኑ ተመላሽይደረጋል፡፡
 7. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ፡ በ0911318856/0911400576 በመደወል መጠየቅ ወይም ከመብራት ሃይል ወደ ኃይሌ ጋርመንት በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው ዋና መ/ቤታችን በአካል በመምጣት  ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

ማይ ዊሽ ኢንተርፕራይዝ  ኃ/የተ/የግ/ማህበር