ሞቲ እንጂነሪንግ በአዲስ አበባ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 02 ለሚገኙት ሶስት ቅርንጫፍ ቢሮዎች (ሪጅናል ቢሮ ወርክ ሾፕና እስቶር ግቢዎች) ደረጃውን የጠበቀ የጥበቃ አገልግሎት አጫርቶ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

Overview

  • Category : Purchases
  • Posted Date : 12/28/2022
  • Phone Number : 0911104044
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 01/23/2023

Description

የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን ሞቲ እንጂነሪንግ በአዲስ አበባ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 02 ለሚገኙት ሶስት ቅርንጫፍ ቢሮዎች (ሪጅናል ቢሮ ወርክ ሾፕና እስቶር ግቢዎች) ደረጃውን የጠበቀ የጥበቃ አገልግሎት አጫርቶ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጥበቃ አገልግሎት ሥራ ዘርፍ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላችሁ ተጫራቾች/ኤጀንሲዎች በጨረታው መሳተፍ የምትችለ መሆኑን እየገለጽን፤ ተፈላጊ የጥበቃ አገልግሎት ዓይነትና የጥራት ደረጃዎች/መሥፈርቶች ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ ከድርጅቱ የግዥ አስተዳደር ቢሮ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡

በተቀመጠው ዝርዝር መሰረት አገልግሎቱን የምታቀርቡበት ዋጋ ቫትን ጨምሮ በምታቀርቡት የጨረታ ሰነድ (ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ሰነድ) ላይ በመጥቀስ በሰም በታሸገ ፓስታ አሽጋችሁ እስከ ታህሳስ 27 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 8.00 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ የዕቃ ግዥ አስተዳደር ቢሮ እንድታስገቡ ተጋብዛችኋል፡፡

አሸናፊ የሚሆነው ተቋም እንደታወቀ ድርጅቱ ባወጣው መስፈርቶችና ጥበቃ ፓሊሲ መሰረት ከድርጅቱ ጋር ውል የሚገባ መሆኑን እያስታወቅን ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ከታህሳስ 19 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ለጨረታው የተጋበዛችሁ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡

ሞቲ እንጂነሪንግ ኃ/የተ/ግ/ማኅበር

አድራሻ፡- ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረጃ 02 ቦሌ መንገድ፤ ሜጋ ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 402

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0911 104044 / 0922 870704 / 0924 974017 መደወል ይችላሉ፡፡