ሪሜምበር ዘ ፑረስት ኮሚዩኒቲ ለቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት የሚያስፈልጉ ልዩ ልዩ ቁሳቁሶች እና መጫወቻ መሳሪያዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት/ማሰራት ይፈልጋል፡፡

remember-the-poorest-community-logo

Overview

 • Category : Stationery Supplies
 • Posted Date : 07/23/2022
 • Phone Number : 0118298298
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 08/05/2022

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ሪሜምበር ዘ ፑረስት ኮሚዩኒቲ በ 1992 ዓ.ም የተመሰረተ እና  በኢ.ፌ.ድ.ሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ አዋጅ ቁጥር 1113/2011 መሰረት በምዝገባ ቁጥር 0727 ዳግም ተመዝግቦ ለችግር የተጋለጡ እናቶችን ና ህፃናትን የመደገፍ ልማት ስራ ላይ የተሰማራ ሀገር በቀል ግብረ-ሰናይ ድርጅት ነው፡፡

ሪሜምበር ዘ ፑረስት ኮሚዩኒቲ  በአዲስ አበባ ከተማ ኣስተዳደር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በወረዳ 14 ልዩ ቦታው ቁሊቲ በተባለ ስፍራ ለቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት የሚያስፈልጉ ልዩ ልዩ ቁሳቁሶች እና መጫወቻ መሳሪያዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት/ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋበዛሉ፡፡

 1. ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት፣ታክስ ክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሳህሊተ ምህረት ቤ/ር ፊት ለ ፊት ቼሻየር ሰርቪስ ኢትዮጵያ 3ኛ ፎቅ በሚገኘው ሪመምበር ዘ ፑረስት ኮሚኒቲ (RPC) ዋናው ቢሮ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘውትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 150.00/አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
 3. ተጫራቾች ከጨረታው በኃላ የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00/ሃያ ሺህ ብር /በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው በባንክ ዋስትና ማሲያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
 4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ዘውትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
 5. ጨረታው የሚቆየው ጋዜጣው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ሲሆን በ ሀምሌ 30 ቀን 2014 ዓ.ም በ 4፡00 ተዘግቶ በዛኑ እለት በ4፡30 ተጨራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሪሜምበር ዘ ፑረስት ኮሚዩኒቲ (RPC) ሳህሊተ ምህረት ቤ/ር ፊት ለ ፊት ቼሻየር ሰርቪስ ኢትዮጵያ 3ኛ ፎቅ በሚገኘው ዋናው ቢሮ ይከፈታል፡፡
 6. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በ ሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 7. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251-118-298-298 ወይም +251-116-733-870 ደውሎ መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡