ሪች ኢትዮጵያ በቲቢ በሽታ ዙሪያ በሬዲዮ ጣቢያው (ኤፍ ኤም ጣቢያው) ተደማጭነትና ተወዳጅነት ባለው በተመረጠ ፕሮግራም ላይ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡

Overview

  • Category : Public Relations & Public Address Systems
  • Posted Date : 07/24/2022
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 08/24/2022

Description

ቀን 27/10/2022ዓ.

 የሬዲዮ አየር ሰዓት ግዢ የጨረታ ማስታወቅያ

ሪች ኢትዮጵያ Stop TB Partnership በገኘው የገንዘብ ድጋፍ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ  ጋር በመተባበር ስለ ቲቢ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ህብረተሰቡ ያለውን ግንዛቤ ከፍ ለማድረግ ይረዳ ዘንድ በቲቢ በሽታ ዙሪያ ከ45-60 ሰከንድ የሚፈጅ  ማስታወቂያ ከነሃሴ 1 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 60 ቀናት በሬዲዮ ጣቢያው (ኤፍ ኤም ጣቢያው) ተደማጭነትና ተወዳጅነት ባለው በተመረጠ ፕሮግራም ላይ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ህጋዊ ፈቃድ ያለው ፣አመታዊ ግብር ስለመገበሩ ማረጋገጫ ያለው ፣ከብሮድካስት ባለስልጣን ፍቃድ ያለው ከዚህ በታች በተዘረዘረው መስፈርት መሰረት መስፈርቱን የሚያሟላ የሚዲያ ድርጅት አወዳድሮ ማስታወቂያውን ለማስተላለፍ ይጋብዛል፡፡

ተጫራቾች አዲስ አበባ ወሎ ሰፈር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት  የጨረታውን ሰነድ /ዶክመንት/ ማግኘት ይችላሉ ::

ስለሆነም ማስታወቅያው የሚቆየው ለ 10 ሳምንት ሆኖ የማስገቢያን ግዜ የሚጨምር ሲሆን ጨረታው የሚጀምረው ይህ ማስታወቅያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መሆኑም እንገልፃለን፡፡

ለበለጠ መረጃ

ወሎ ሰፈር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት KT-12 ህንፃ 5ኛ ፎቅ በአካል በመገኘት ማግኘት ይችላሉ::

ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡