ራስ አገዝ የሴቶች ድርጅት (ራሴድ)ለተጎዱ የድርጅቱ አባላት (ተጠቃሚ) ድጋፍ ለማድረግ 120 ኩንታል 1ኛ ደረጃ ሰርገኛ ጤፍ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

Overview

 • Category : Agriculture Farm Products
 • Posted Date : 07/10/2021
 • Phone Number : 0911621287
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 07/16/2021

Description

የጤፍ ግዢ ጨረታ ማስታወቂያ

ራስ አገዝ የሴቶች ድርጅት (ራሴድ) ከአውሮፓ ህብረት ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ንግዳቸው ለቀዘቀዘባቸው እና ለተጎዱ የድርጅቱ አባላት (ተጠቃሚ) ድጋፍ ለማድረግ 120 ኩንታል 1ኛ ደረጃ ሰርገኛ ጤፍ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ

 1. የጤፍ ሽያጭ ንግድ ፈቃድ ያለው ፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው እና የዘመኑን የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል እንዲሁም ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል፡፡
 2. ተጫራቾች የትራንስፖርትና የማዉረጃ ጉልበት ዋጋን እንዲሁም አስፈላጊውን የመንግስት ታክስ ጨምሮ አንድ ኩንታል አንደኛ ደረጃ ሰርገኛ ጤፍ የሚያቀርቡበትን ዋጋ በግልጽ በመሙላት እንዲሁም አጠቃላይ የ120 ኩንታል አንደኛ ደረጃ ሰርገኛ ጤፍ ጥቅል ዋጋን አስልቶ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 3. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለትመቶ/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 የስራ ቀናት ውስጥ ዘውትር በስራ ሰዓት ሳሪስ ሀኪም ማሞ ሰፈር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት ቢሮ ቁጥር 33 መግዛት ይችላሉ፡፡
 4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ከአንደኛ ደረጃ ሰርገኛ ጤፍ ናሙና ግማሽ ኪሎ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያቀርቡት ገንዘብ ጠቅላላ ካቀረቡት የመሸጫ ዋጋ 5% (አምስት በመቶ) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ሲሆን በድርጅቱ ስም (Organization for Women In Self Employment) በሚል በማሰራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 6. አሸናፊው ተጫራች የሚያቀርበው ሰርግኛ ጤፍ ለድርጅቱ በሚያመቸው ቦታ ላይ ሲሆን እያንዳንዱን መቶ ኪሎ ለሁለት እያካፈለ በሃምሳ ኪሎ በማድረግ ለተጠቃሚዎቹ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡ 120 ኩንታል ተጠቃሎ ሲቀርብና በተባለው ቦታ ለተጠቃሚዎቹ ማስረከቡ ሲረጋገጥ የተያዘው 5% C.P.O ጭምር ለአሸናፊው ተጫራች ይከፈላል፡፡
 7. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለው 5ተኛ የስራ ቀን ከሰአት በኃላ 8፡00 ሰዓት ላይ ሳሪስ ሀኪም ማሞ ሰፈር በሚገኘው የድርጅቱ ስብሰባ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
 8. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በቢሮ ስልክ ቁጥር  0911621287/0114423587 መጠየቅ ይችላሉ፡፡ 

Send me an email when this category has been updated