ሮፋም ማኑፋክቸሪንግ እና ሰርቪስ ኃ/የተ/የግ/ማ ለሚያስተዳድራቸው ከቅድመ መደበኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ለ2015 ዓ.ም የት/ት ዘመን የተለያዩ የጽህፈት መሳፈሪያዎችና ግብአቶች፣ኮምፒዩተሮች፣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Overview

 • Category : Computer Purchase
 • Posted Date : 07/30/2022
 • Phone Number : 0988501004
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 08/11/2022

Description

ሮፋም ማኑፋክቸሪንግ እና ሰርቪስ /የተ/የግ/

የጨረታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን ለሚያስተዳድራቸው ከቅድመ መደበኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ለ2015 ዓ.ም የት/ት ዘመን

1ኛ/ የተለያዩ የጽህፈት መሳፈሪያዎችና ግብአቶች፣

2ኛ/ የጽዳት እቃዎች፣

3ኛ/ የስፖርት ትጥቆችና ግብአቶች፣

4ኛ/ ኮምፒዩተሮች፣

በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት  በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለጸውነ መስፈርት በማሟላት በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

 1. ተጫራቾች በመስኩ የተሰጠ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት፣ እንዲሁም ከገቢዎች ሚ/ር በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ክሊራንስ ማቅረብ አለባቸው፡፡
 2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በእያንዳንዱ አቅርቦት (ጥቅል) 10,000.00(አስር ሺህ ብር) በሮፋም ማኑፋክቸሪንግ እና ሰርቪስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ(CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 3. ተጫራቾች ስለጨረታው የሚገልጸውን ሰነድ ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ አጠገብ ወይም ሂል ሳይድ ጎን ከሚገኘው ሰላም ህጻናት መንደር ግቢ ውስጥ ሮፋም ማኑፋክቸሪንግ እና ሰርቪስ አስተዳደር ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
 4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ እና ቴክኒካል ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከሀምሌ 25 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ነሀሴ 3 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 5. ጨረታው ነሀሴ 4 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
 6. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0988501004 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
 7. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡

ሮፋም ማኑፋክቸሪንግና ሰርቪስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

ከሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ አጠገብ ወይም ሂል ሳይድ ት/ቤት ወደ ውስጥ በሚያስገባው ኮብል እስቶን ገባ ብሎ በሚገኘው ሰላም ህጻናት መንደር ግቢ ውስጥ፡፡