ሰላም የህዝብ ማመላለሻ አ/ማ 13ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ

Overview

  • Category : Announcement
  • Posted Date : 11/07/2022
  • Phone Number : 0911466187
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 12/03/2022

Description

ማስታወቂያ

የባለአክሲዮኖች 13ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ

ሰላም የህዝብ ማመላለሻ አ/ማ 13ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ቅዳሜ ህዳር 24/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በግዮን ሆቴል ያካሂዳል፡፡ ስለሆነም ባለአክስዮኖች ወይም ህጋዊ ውክልና ያላቸው አካላት በተጠቀሰው ቦታ፣ ቀንና ሰዓት በመገኘት የጉባኤ ተሳታፊ እንዲሆኑ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን በአክብሮት ያቀርባል፡፡

የጉባኤው አጀንዳዎች፡-

  1. የ2012፣ 2013 እና 2014 በጀት ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርትን ማዳመጥ
  2. የውጭ ኦዲተሮች ሪፖርትን ማዳመጥ
  3. በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ መወያየት
  4. አዳዲስ ኦዲተሮችን መሰየም
  5. አዳዲስ የቦርድ አመራሮችን ማስመረጥ

ማሳሰቢያ፡-

በጉባኤው ላይ በግንባር መገኘት የማትችሉ ባለአክስዮኖች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት አንስቶ እስከ ህዳር 20 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ መስቀል አደባባይ ፊንፍኔ ሕንጻ በሚገኘው የኩባንያው ዋና መስሪያ ቤት 6ኛ ፎቅ በመቅረብ ኩባንያው ባዘጋጀው የውክልና ቅጽ ላይ ለመሙላት የባለአክስዮኖች ህጋዊ ተወካዮች አግባብነት ካለው የመንግስት አካል የተሰጠ የውክልና ስልጣን ሰነድ ይዛችሁ በመቅረብ በጉባኤው ላይ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡

ጉባኤው ተወያይቶ የሚያስተላልፋቸው ውሳኔዎች ባልተገኙ አባላት ላይ የፀና ይሆናል፡፡

የዳይሬክተሮች ቦርድ

ሰላም የህዝብ ማመላለሻ አክስዮን ማህበር

ለተጨማሪ መረጃ፡-

ስልክ 251-11-470-83-32   ስልክ ቁጥር 09 11 46 61 87

Email:selam.bus@ethionet.et                          Website:Selambus.com

* 101011  አዲስ አበባ ኢትዮጵያ