ሰላም የህጻናት መንደር ያገለገሉ መኪኖች፤ ኢንጂኖች፤ የመኪና ቅሪት አካልና የተለያዩ ብረታብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በነጠላና በአንድነት በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Selam-Childrens-Village-logo-1

Overview

  • Category : Disposal Sale
  • Posted Date : 03/28/2021
  • Phone Number : 0116462942
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 04/07/2021

Description

ሠላም ህጻናት መንደር

የጨረታ ማስታወቂያ

 

ድርጅታችን ሰላም የህጻናት መንደር በዋና መ/ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ያሉ ያገለገሉ መኪኖች፤ ኢንጂኖች፤ የመኪና ቅሪት አካልና የተለያዩ ብረታብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በነጠላና በአንድነት በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለሰባት ተከታታይ የሥራ ቀናት (ከሰኞ እስከ አርብ) ድረስ ከጠዋቱ 3፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ድረስ ከዋናው መ/ቤት ፋይናንስ መምሪያ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል መግዛትና ንብረቶቹን መመልከት ይችላሉ፡፡

  1. ተጫራቾች እንደ ጨረታው አቀራረብ ንብረቶቹን የሚገዙበትን ዋጋ  በታሸገ ፖስታ በጨረታው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾችየሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ (10%) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ያስያዙት  የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ የጨረታው ውጤት ከተገለጸ በኃላ ለተሸናፊ ተጫራቾች ተመላሽ ይደረጋል፡፡
  3. ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በጨረታው ያሸነፉትን ዕቃ ዋጋውን በአንዴ ከፍለዉ በአምስት (5) የሥራ ቀናት  ውስጥ ንብረቱን የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡
  4. በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች ካላነሱ ለጨረታው ያስያዙት ቢድ ቦንድ ለድርጅቱ ገቢ ተደርጎ ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
  5. በጨረታው ያሸነፉ ተጫራቾች የገዙትን ንብረቶች ለማራገፍ፤ ለማስጫን እና ልዩ ልዩ ወጪዎች ቢኖሩ በጨረታው አሸናፊ የሚከፈሉ ይሆናሉ፡፡

ጨረታው ተጫራቾች በተገኙበት መጋቢት 29 ቀን 2012 ዓ.ም. ጠዋት 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ረቡዕ መጋቢት 29 ቀን 2013 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡30 ይከፈታል፡፡

ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡®  ኮተቤ ሃና ማርያም ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ፤ ስልክ ® 011-646-29-42

ድርጅቱ

 

 

 

Send me an email when this category has been updated