ሰበታ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር ያገለገሉ የተለያዩ ዓይነት ዕቃዎች ማለትም ብረታ ብረት፣ የብረት በርሜሎች፣ ጀሪካኖች፣ የወተት ማሸጊያ ላስቲኮች፣ የአሞኒያ ሲሊንደሮች፣ና ሌሎች የተለያዩ ያገለገሉ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

Overview

 • Category : Other Sale
 • Posted Date : 09/24/2022
 • Phone Number : 0113665594
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 10/18/2022

Description

ያገለገሉ ዕቃዎች የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር 001/15  

ድርጅቱ ያገለገሉ የተለያዩ ዓይነት ዕቃዎች ማለትም ብረታ ብረት፣ የብረት በርሜሎች፣ ጀሪካኖች፣ የወተት ማሸጊያ ላስቲኮች፣ የአሞኒያ ሲሊንደሮች፣ የውሃ ማጠራቀሚያዎች፣ የአይሱዙ ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ ጎማዎችና ቸርኬዎች፣ ባትሪዎች፣የተቃጠለ ዘይትና ሌሎች የተለያዩ ያገለገሉ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም፡-

 • በጨረታ መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት በጨረታ የመሳተፍ መብቱ ነው፡፡
 • ተጫራቾች የአገለገሉ ዕቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ በጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
 • ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሰበታ ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ብር 00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
 • ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን ዕቃዎች ሰበታ/አለም ገና/ በድርጅቱ መጋዘን ዘወትር በሥራ ቀን ከሰኞ እስከ ዓርብ ጠዋት 2፡30 – 6፡00 ሰዓት፣ ከሰዓት በኃላ 7፡00 -10፡00 ሰዓት፣ቅዳሜ ጠዋት 2፡30 – 6፡00 ሰዓት በመገኘት መመልከት ይችላሉ፡፡
 • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) በጥሬ ገንዘብ ወይም ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡
 • ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ዋጋ በስም በታሸገ ፖስታ እስከ ጥቅምት 8 ቀን 2015 ዓ.ም 4፡00 ድረስ በድርጅቱ ዋና መ/ቤት ሽያጭ ዋና ክፍል ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 • ጨረታው ጥቅምት 8 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በእለቱ ከቀኑ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
 • የጨረታ አሸናፊ የሚሆነው በተናጠል ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ይሆናል፡፡
 • ተጫራቾች በጨረታ ማስገቢያ የታሸገ ፓስታ ላይ ስም፣ ፊርማና የስልክ ቁጥር መፃፍ አለባቸው፡፡
 • ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 • ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለጋቸው በሚከተለው አድራሻ በመደወል ወይም በአካል በመገኘት መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ስልክ ቁጥር 011-3-665594/011-3-662066

ሰበታ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር

አድራሻ፡- አለም ገና ከሚካኤል ቤ/ክርስቲያን ወረድ ብሎ ሰበታ መንገድ