ሰበታ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እ.ኤ.አ የ2022፣2023 እና 2024 በጀት ዓመት ለሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ሂሳቡን የሚመረምሩለትን የውጭ ኦዲተሮችን አወዳድሮ መሰየም ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : Auditing Related
- Posted Date : 02/13/2022
- Phone Number : 0113384105
- Source : Reporter
- Closing Date : 02/25/2022
Description
የኦዲት ጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ሰበታ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እ.ኤ.አ የ2022፣2023 እና 2024 በጀት ዓመት ለሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ሂሳቡን የሚመረምሩለትን የውጭ ኦዲተሮችን አወዳድሮ መሰየም ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም፡-
- ከኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ለ2014 የታደሠ የድርጅት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው፣
- ለ2014 የታደሠ የንግድ ፈቃድ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN ያለው፣
- ከዚህ በፊት ከሰሩባቸው ድርጅቶች አፈፃፀማቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ለሥራው የሚመድቧቸውን ባለሙያዎች ብዛትና የትምህርት ደረጃ እንዲሁም ለውድድሩ አስፈላጊ የሆኑ ማስረጃዎችን በማያያዝ ፋይናንሽያል እና ቴክኒካል ሰነዶችን በማዘጋጀት ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ከሰኞ – አርብ ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ሰነዶቻችሁን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ አለምገና ሰበታ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ወረድ ብሎ በሚገኘው ዋናው ፋብሪካ በአካል በመቅረብ እንድታስገቡ እናሳስባለን፡፡
ለበለጠ መረጃ፡-
0113 38 41 05/0113 66 53 67/0113 66 23 81/011 3 38 41 06
ሰበታ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር