ሲራሮ ሕጻናትና ቤተሰብ ልማት ማህበር 1000/አንድ ሺህ/ ኩንታል ጥራቱን የጠበቀ የምግብ ቦቆሎ እህል በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

Overview

  • Category : Flora & Horticulture
  • Posted Date : 06/03/2021
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 06/14/2021

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ሲራሮ ሕጻናትና ቤተሰብ ልማት ማህበር/Siraro child and Family development Association/ መንግስታዊ ያልሆነ የበጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን የማህበረሰቡን ፍላጎት መሠረት አድርጎ በትምህርት፤በጠና ፤ በምግብ ዋስትናና ገቢ ማስገኛ ፤ በዉኃ እና ሳኒተሸን በመሳሰሉት የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ይሰራል፡፡

ድርጅታችን በዘንድሮ ዓመት በድርቅ ምክንያት ለምግብ ዕጥረት የተጋለጡትን ማህበረሰብ ለመደገፍ 1000/አንድ ሺህ/ ኩንታል ጥራቱን የጠበቀ የምግብ ቦቆሎ እህል በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ሰለሆነም በእህል ንግድ ዘርፍ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ እና መሥፈርቱን የሚያሟሉ ድርጅቶች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7/ሰባት/ተከታታይ የሥራ ቀናትና የሥራ ሰዓት ከዚህ በታች በተመለከተዉ የድርጅታችን አድራሻ በማይመለስ 200/ሁለት መቶ ብር/ ዝርዝር የጨረታዉን ሰነድ በመግዛት መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እናሳስባለን፡፡

አድራሻ፡ ሲራሮ ሕጻናትና ቤተሰብ ልማት ማህበር/Siraro child and Family development Association/ ኦሮሚያ ክልል፤ሻሽመኔ ከተማ፤ በተለምዶ ሞቢል በሚባል አካባቢ አዋሽ ባንክ ሕንጻ፤3ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 1 ነዉ፡፡ ጨረታዉ የሚከፈተዉ ጨረታዉ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የሥራ ቀናት በ7ኛ የሥራ ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት በጨረታዉ አከፋፈት ላይ ለመገኘት ፈቃደኛ በሆኑ ተሳታፊዎች ባሉበት ሲሆን ቦታዉም የቸረታ ሰነዱ የተገዛበት ቢሮ ዉስጥ ይሆናል፡፡ 

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፍልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡

ድርጅቱ