ሲራሮ ሕጻናትና ቤተሰብ ልማት ማህበር/Siraro child and Family development Association/ በድርቅ ምክንያት ለምግብ ዕጥረት የተጋለጡትን ማህበረሰብ ለመደገፍ 900/ዘጠኝ መቶ/ ኩንታል ጥራቱን የጠበቀ ለሰዉ ምግብነት የሚዉል ጥሬ የምግብ ቦቆሎ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : Flora & Horticulture
- Posted Date : 07/17/2022
- Closing Date : 07/26/2022
- Source : Reporter
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ሲራሮ ሕጻናትና ቤተሰብ ልማት ማህበር/Siraro child and Family development Association/ መንግስታዊ ያልሆነ የበጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን የማህበረሰቡን ፍላጎት መሠረት አድርጎ በትምህርት፤በጠና ፤ በምግብ ዋስትናና ገቢ ማስገኛ ፤ በዉኃ እና ሳኒተሸን በመሳሰሉት የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ይሰራል፡፡
ድርጅታችን በዘንድሮ ዓመት በ2014 ዓ/ም በድርቅ ምክንያት ለምግብ ዕጥረት የተጋለጡትን ማህበረሰብ ለመደገፍ 900/ዘጠኝ መቶ/ ኩንታል ጥራቱን የጠበቀ ለሰዉ ምግብነት የሚዉል ጥሬ የምግብ ቦቆሎ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ሰለሆነም በእህል ንግድ ዘርፍ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ እና መሥፈርቱን የሚያሟሉ ድርጅቶች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7/ሰባት/ተከታታይ የሥራ ቀናትና የሥራ ሰዓት ከዚህ በታች በተመለከተዉ የድርጅታችን አድራሻ በማይመለስ 500/አምስት መቶ ብር/ ዝርዝር የጨረታዉን ሰነድ በመግዛት መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እናሳስባለን፡፡
አድራሻ፡ ሲራሮ ሕጻናትና ቤተሰብ ልማት ማህበር/Siraro child and Family development Association/ ኦሮሚያ ክልል፤ሻሽመኔ ከተማ፤ በተለምዶ ሞቢል በሚባል አካባቢ አዋሽ ባንክ ሕንጻ፤3ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 1 ነዉ፡፡ ጨረታዉ የሚከፈተዉ ጨረታዉ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የሥራ ቀናት በ7ኛ የሥራ ቀን ከቀኑ በ10፡00 ሰዓት(ሐምሌ 19 ቀን 2014 ዓ/ም) በጨረታዉ አከፋፈት ላይ ለመገኘት ፈቃደኛ በሆኑ ተሳታፊዎች ባሉበት ሲሆን ቦታዉም የጨረታ ሰነዱ የተገዛበት ቢሮ ዉስጥ ይሆናል፡፡
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፍልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
ድርጅቱ