ሲዳማ  ተራ ህንጻ ሥራ አክስዮን ማህበር የጥበቃ እና የጽዳት አገልግሎት አወዳድሮ ከአሸናፊው ኤጀንሲ ጋር የሥራ ውል በመዋዋል ማሰራት ይፈልጋል፡፡

Overview

 • Category : Cleaning & Janitorial Service
 • Posted Date : 09/24/2021
 • Phone Number : 0118333792
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 10/16/2021

Description

ሲዳማ ተራ ህንጻ አክስዮን ማህበር

የጥበቃ እና የጽዳት አገልግሎት ግዢ ጨረታ ማስታወቂያ

ሲዳማ  ተራ ህንጻ ሥራ አክስዮን ማህበር የጥበቃ እና የጽዳት አገልግሎት አወዳድሮ ከአሸናፊው ኤጀንሲ ጋር የሥራ ውል በመዋዋል ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም አገልግሎቱን ለማቅረብ ፍላጎቱና ብቃቱ ያላችሁ ኤጀንሲዎች የሚከተሉትን የጨረታ መመሪያዎችን በማሟላት በጨረታው እንድትሳተፉ እንጋብዛለን፡፡

 1. ተጫራቾች በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክት ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት እና የተጨማሪ እሴት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
 2. ተጫራቾች እንደየፍላጎታቸው ለጥበቃ ወይም ለጽዳት ወይም ለሁለቱም መወዳደር ይችላሉ፡፡
 3. ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀው ሰነድ ከነመመሪያው የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ከኩባንያው ዋና መ/ቤት ብሎክ 3-6ኛ ፎቅ የክፍል ቁጥር 609 መውሰድ ይችላሉ፡፡
 4. ተጫራቾች በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ይሆን ዘንድ ብር 40,000 (አርባ ሺህ ብር) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም የባንክ ዋስትና ማረጋገጫ ደብዳቤ ይዘው መቅረብ ይገባቸዋል፡፡
 5. ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ሃሳባቸውን በጨረታው መመሪያው መሠረት ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በማለት በግልጽ ከፋፍለው በተለያዩ ፖስታዎች አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 6. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ከመስከረም 18 ቀን 2014 ዓ.ም. እስከ ጥቅምት 06 ቀን 2014 ዓ.ም. 4፡00 ሰዓት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ ልክ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋናው መ/ቤት ይከፈታል፡፡
 7. አሸናፊው ተጫራች ጨረታውን ማሸነፉን በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ በአምስት የሥራ ቀናት ውስጥ የሥራ ውል መዋዋል ይጠበቅበታል፡፡ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርቦ ውል ካልተፈራረመ ጨረታውን እንዳልፈለገው ተቆጥሮ ያስያዘውን የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይደረጋል፡፡
 8. በሌሎች ተወዳዳሪዎች ዋጋ ወይም ሁኔታ ላይ ተመርኩዞ ዋጋ መስጠት አይቻልም፡፡
 9. ድርጅቱ ጨረታው በሙሉም ሆነ በከፊል ከመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 10. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0118-33-37-92 ወይም 0984-87-84-94 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

ስዳሞ ተራ ህንጻ ሥራ አክስዮን ማህበር

መርካቶ ሲኒማ ራስ አጠገብ