ሲዳሞ ተራ ህንጻ ሥራ አክስዮን ማህበር ባሰስገነባው 2B+G+10 ቅይጥ አገልግሎት ህንጻ ብሎክ 1 ከ6ኛ እስከ 9ኛ ፎቅ ድረስ የሚገኙና ለመኝታ አገልግሎት የሚውሉ 72 (ሰባ ሁለት) ክፍሎችን እንዲሁም 10ኛ ፎቅ ላይ ለባርና ለሬስቶራንት ታስቦ የተዘጋጀውን ቦታ ጨምሮ ባሉበት ሁኔታ አንድ ላይ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡

Overview

 • Category : House & Building Rent
 • Posted Date : 07/02/2021
 • Phone Number : 0984878494
 • Source : Reporter
 • Closing Date : 07/28/2021

Description

የሆቴል ክፍሎች ጨረታ ማስታወቂያ

ሲዳሞ ተራ ህንጻ ሥራ አክስዮን ማህበር በሊዝ ደንብ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚያገኛቸውን ቦታዎችን መልሶ በማልማት ለኪራይና ለሽያጭ የሚያቀርብ የሪል እስቴት አክስዮን ማህበር ነው ፡፡ ማህበሩ በአሁኑ ወቅት መርካቶ ሲኒማ ራስ አጠገብ ሶስት ዘመናዊ ቅይጥ አገልግሎት የሚሰጡ ህንጻዎችን ገንብቶ ለአገልግሎት ያበቃ ሲሆን በርካታ ለንግድ ሱቆች፤ ለመጋዝኖች፤ ለቢሮና ለሆቴል አገልግሎት የሚሆኑ ክፍሎችን በማከራየት ላይ ይገኛል፡፡

ይህ በእንዲህ እያለ አክስዮን ማህበሩ ባሰስገነባው 2B+G+10 ቅይጥ አገልግሎት ህንጻ ብሎክ 1 ከ6ኛ እስከ 9ኛ ፎቅ ድረስ የሚገኙና ለመኝታ አገልግሎት የሚውሉ 72 (ሰባ ሁለት) ክፍሎችን እንዲሁም 10ኛ ፎቅ ላይ ለባርና ለሬስቶራንት ታስቦ የተዘጋጀውን ቦታ ጨምሮ ባሉበት ሁኔታ አንድ ላይ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፤

 1. ተጫራቾች በጨረታው ላይ ለመሳተፍ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት እና የተጨማሪ እሴት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
 2. ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀው ሰነድ ከነመመሪያው የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ከታች በተራ ቁጥር 5 በተጠቀሰው መሠረት እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ከኩባንያው ዋና መ/ቤት ብሎክ 3 6ኛ ፎቅ ክፍል ቁጥር 609 መውሰድ ይችላሉ፡፡
 3. ተጫራቾች በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) ይዘው መቅረብ ይገባቸዋል፡፡ ጨረታውን ላላሸነፉ ተወዳዳሪዎች የጨረታ አጠቃላይ ውጤት ከታወቀ በኃላ ዋስትናው ይመለስላቸዋል፡፡
 4. የጨረታው አሸናፊ ውድድሩ ማሸነፉን ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ የሚፈለግበትን ክፍያ ሁሉ አጠናቅቆ ውል መፈራረም አለበት፡፡ በዚህ ጊዜ ገደብ ውስጥ ክፍያውን አጠናቆ ውል ካልተፈራረመ ጨረታውን እንዳልፈለገው ተቆጥሮ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ለማህበሩ ገቢ ይደረጋል፡፡
 5. ተጫራቾችየጨረታዋጋየሞሉበትፎርምእናሌሎችበተራቁጥር 1 እና 2 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች እንዲሁም በዘርፉ የሥራ ልምድ ካላቸው ይህንኑ አያይዘው በሰም በታሸገኢንቬሎፕማቅረብአለባቸው፡፡
 6. የጨረታሰነድየማስገቢያጊዜከሰኔ 28 ቀን 2013 እስከሀምሌ 21 ቀን 2013 ዓ.ምከቀኑ 8፡00 ሰዓትድረስይሆናል፡፡ ከቀኑ 8፡00 በኃላዘግይተውየሚቀርቡየጨረታሰነዶችበተቀባይነትየላቸውም፡፡ ጨረታውበተመሳሳይቀን 8፡30 ላይተጫራቾችወይምህጋዊወኪሎቻቸውበተገኙበትበዋናው መ/ቤትይከፈታል፡፡
 7. በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም፡፡
 8. ተጫራቾች በሥራ ሰዓት ህንጻውንና የክፍሎቹን መጎብኘት ይችላሉ፡፡
 9. ኩባንያው ጨረታው በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 10. ለተጨማሪ ማብራሪያ 0984-87-84-94//0916-01-42-97 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

ሲዳሞ ተራ ህንጻ ሥራ አክስዮን ማህበር – አዲስ አበባ

Send me an email when this category has been updated