ሲዳሞ ተራ ህንፃ ሥራ አክስዮን ማህበር በግንባታ ሂደት ላይ ለሚገኘው ህንፃ ስራ ማስጀመሪያ የተለያዩ ዕቃዎች ግዥና የአልሙንየም ስራዎችን በሚቀርበው ዝርዝር መሰረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

Overview

  • Category : Aluminum Related Products Supply & Sale
  • Posted Date : 11/21/2022
  • Phone Number : 0112733037
  • Source : Reporter
  • Closing Date : 12/02/2022

Description

ሲዳሞ ተራ ህንፃ ሥራ አክስዮን ማህበር

የጨረታ ማስታወቂያ

አክስዮን ማህበራችን በግንባታ ሂደት ላይ ለሚገኘው ህንፃ ስራ ማስጀመሪያ የተለያዩ ዕቃዎች ግዥና የአልሙንየም ስራዎችን በሚቀርበው ዝርዝር መሰረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

  1. የኤሌክትሪክ እቃዎች ግዢ
  2. ለመኝታ ቤት አገልግሎት ማስጀመሪያ የሚውሉ ዕቃዎች
  3. የተለያዩ የአልሙንየም ስራዎች

ስለሆነም ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 50.00 /ሃምሳ/ ብቻ ከፍለው ከማህበሩ አስተዳርና ፋይናንስ መምሪያ በመውሰድ በተያያዘው ዝርዝር መሰረት የሚያቀርቡበትን/ የሚሰሩበትን ዋጋ በመሙላት በፖስታ አሽገው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15/አስራ አምስት/ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ ለዚሁ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ጨረታው ሰኞ ህዳር 26 ቀን 2015 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ይዘጋል፡፡ በተራ ቁጥር 1 እና 2 ለተጠቀሱት የፋይናንሻል ሰነድ እንዲሁም የአልሙኒየም ሥራ ቴክኒካል ዶክመንቱ በዕለቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን የፋይናንሻል ሰነድ የሚከፈትበት ቀን በውስጥ ማስታወቂያ የሚገለጽ ይሆናል፡፡

ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርት፡-

1.ተጫራቾች ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤የዘመኑን ግብር ግብር የከፈሉ፤ተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ እና የግብር ከፋይ ማስረጃቸውን ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

2.ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆናቸውን የሚገልጽ ታክስ ክሊራንስ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት ማቅረብ አለባቸው፡፡

3.ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን ለኤሌክትሪክ እቃዎች ብር 10,000.00 (አስር ሺህ)፣ለመኝታ ቤት ዕቃዎች ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)፣ ለአልሙኒየም ስራዎች ብር 80,000.00 (ሰማንያ ሺህ) መሆን አለበት፡፡

4.ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ በመሙላት የድርጅቱን ማህተም፣ፊርማ እና ሙሉ ስም እንዲሁም አድራሻቸውን በመግለፅ በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

5.ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉት በዘርፉ ፈቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡

6.ለአልሙኒየም ሥራዎች ተጫራቾች ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነዱ ለየብቻ ታሽጎ መቅረብ አለበት፡፡

8.ጨረታውን አሸናፊ ሆነው ሲገኙ ከጠቅላላ ዋጋው 10% የመልካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና ማስያዝ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

  1. ማህበሩ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡

አድራሻ፡ መርካቶ ሲኒማ ራስ ሲዳሞ ተራ ህንፃ ሥራ አ.ማ ህንፃ ቁጥር 3 ስድስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር     609

   ስልክ ቁጥር 011 273 30 37       ለተጨማሪ መረጃ 0901 00 62 41