ሴንድ ኤ ካዉ ኢትዮጵያ በወላይታ ዞን ፡ ሶዶ ዙሪያ ወረዳ፡ ጉሩሞ ውይዴ ቀበሌ አንድ የንጹህ መጠጥ ውሃ ምንጭ የማጎልበት ሥራ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
Overview
- Category : Water Well Drilling & Water System Installation
- Posted Date : 07/27/2022
- Phone Number : 0461804011
- Source : Reporter
- Closing Date : 08/05/2022
Description
ለምንጭ ማጎልበት የወጣ የጨረታ ማሰታወቂያ
ድርጀታችን ሴንድ ኤ ካዉ ኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎችና ዞኖች በርካታ የልማት ሥራዎችን እየሠራ ይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ድርጅታችን በወላይታ ዞን ፡ ሶዶ ዙሪያ ወረዳ፡ ጉሩሞ ውይዴ ቀበሌ አንድ የንጹህ መጠጥ ውሃ ምንጭ የማጎልበት ሥራ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች ወይም ተጫራቾች መሳተፍ እንደምትችሉ እንገልጻለን፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና የ2014 ዓ.ም ንግድ ፈቃድ ያሳደሱ፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ/VAT/ ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር/TIN NUMBER/ያለቸው፡፡
- ተጫራቾች GC ደረጃ 6 ወይንም WWC ደረጃ 6 እና ከዚያ በላይ ያላቸዉ መሆን አለባቸዉ፡፡
- የጨረታዉን ማሰከበሪያ (CPO) 10,000/አስር ሺህ ብር/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ከሥራው ጋር ተያያዥነት ያለዉ ከዚህ ቀደም የሰሩበትን ሁለትና ከዚያ በላይ የመልካም ሥራ አፈጻጸም የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታዉን ሰነድ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ዋናዉንና ኮፒዉን በሰም በታሸገ እንቭሎፕ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- የጨረታ ማስገቢያው ሃሙስ ሃምሌ 28 2014 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 የሚያበቃ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 4፡15 የሚከፈት ይሆናል፡፡
- የጨረታዉ አሸናፊ ከተገለፀ በኃላ አሸናፊው ተጫራች በ2/ሁለት/ ቀናት ዉሰጥ በአካል በመቅረብ ዉል መፈፀም አለበት፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ለጨረታዉ ያስያዙት የጨረታ ማሰከበሪያ ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የመስክ/ሳይት ምልከታ ማድረግና ከቀበሌው ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 7 /ሰባት/ የስራ ቀናት ብቻ አየር ላይ የሚቆይ ይሆናል፡
- ማሳሰቢያ፡ የጨረታ ሰነዱን ወላይታ ሶዶ ሉትራን/አሜሪካን ኢንተርናሽናል አካዳሚ ትምህርት ቤት ፊትለፊት በሚገኘው የሴንድ ኤ ካው ኢትዮጵያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት በስራ ቀንና ሰአት በመምጣት መውሰድ ይቻላል፡ የጨረታ ሰንድ ማስገቢያው ስፍራውም በዚሁ ከላይ በተጠቀሰው የድርጅቱ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ይሆናል።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0461804011/0461804463
ወይም በሞባይል ቁጥር 0920174027/0911319367 በመደወል መረጃ ማግኘት የምትችሉ
መሆኑን እንገልጻለን፡፡